Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 23:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በሰማርያም ከተሞች የነበሩትን፥ እግዚአብሔርን ያስቈጡት ዘንድ የእስራኤል ነገሥታት የሠሩትን የኮረብታውን መስገጃዎች ኢዮስያስ አስወገዳቸው፤ በቤቴልም እንዳደረገው ነገር ሁሉ እንዲሁ አደረገባቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ኢዮስያስም በቤቴል እንዳደረገው ሁሉ በሰማርያም ከተሞች ኰረብቶች ላይ የእስራኤል ነገሥታት አሠርተዋቸው የነበሩትንና እግዚአብሔርን ያስቈጡበትን ቤተ ጣዖቶች ሁሉ አስወገደ፤ አረከሳቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ንጉሥ ኢዮስያስ በማንኛይቱም የእስራኤል ከተማ የእስራኤል ነገሥታት አሠርተዋቸው የነበሩትን የእግዚአብሔርን ቁጣ ለማነሣሣት ምክንያት የሆኑትን የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን ሁሉ አፈራረሰ፤ በቤትኤል ያደረገውን ሁሉ በእነዚያ መሠዊያዎች ላይ ፈጸመ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ንጉሥ ኢዮስያስ በማንኛይቱም የእስራኤል ከተማ የእስራኤል ነገሥታት አሠርተዋቸው የነበሩትን የእግዚአብሔርን ቊጣ ለማነሣሣት ምክንያት የሆኑትን የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን ሁሉ አፈራረሰ፤ በቤትኤል ያደረገውን ሁሉ በእነዚያ መሠዊያዎች ላይ ፈጸመ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በሰ​ማ​ር​ያም ከተ​ሞች የነ​በ​ሩ​ትን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያስ​ቈ​ጡት ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የሠ​ሩ​ትን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች ኢዮ​ስ​ያስ አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው፤ በቤ​ቴ​ልም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ነገር ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 23:19
14 交叉引用  

በኮረብቶቹም ላይ መስገጃዎች ሠራ፤ ከሌዊ ልጆች ካይደሉ ከሕዝብ ሁሉ ካህናትን አደረገ።


በቤቴል ባለው መሠዊያ ላይ፥ በሰማርያም ከተሞች ውስጥ ባሉ በኮረብታዎቹ መስገጃዎች ላይ በእግዚአብሔር ቃል የጮኸው ነገር በእውነት ይደርሳልና።”


አክዓብም የማምለኪያ ዐፀድ ተከለ፤ አክዓብም ከእርሱ በፊት ከነበሩት ሁሉ ይልቅ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚያስቆጣውን ነገር አበዛ።


የእስራኤልም ልጆች በአምላካቸው በእግዚአብሔር ላይ ቅን ያልሆነውን ንገር በስውር አደረጉ፤ በከተሞቻቸውም ሁሉ ከዘበኞች ግንብ ጀምሮ እስከ ተመሸገች ከተማ ድረስ በከፍታዎቹ ላይ መስገጃዎችን ሠሩ።


ልጁንም በእሳት አሳለፈ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፤ አስማትም አደረገ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ።


የአክዓብንም ልጅ አግብቶ ነበርና የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ።


ይህም ሁሉ በተፈጸመ ጊዜ በዚያ የተገኙ እስራኤል ሁሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው ሁሉን ፈጽመው እስካጠፉአቸው ድረስ ሐውልቶቹን ሰባበሩ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጡ፤ በይሁዳና በብንያምም ሁሉ ደግሞም በኤፍሬምና በምናሴ የነበሩትን የኮረብታው መስገጃዎችና መሠዊያዎች አፈረሱ። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስታቸውና ወደ ከተሞቻቸው ተመለሱ።


አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


跟着我们:

广告


广告