Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 23:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የይሁዳም ነገሥታት በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ አጠገብ በከተማው አቅራቢያ በነበረው በጃንደረባው በናታንሜሌክ መኖሪያ አጠገብ ለፀሐይ የሰጡትን ፈረሶች አስወገደ፤ የፀሐይንም ሠረገሎች በእሳት አቃጠለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የይሁዳ ነገሥታት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መግቢያ ላይ ለፀሓይ አምልኮ የሰጧቸውን ፈረሶች ከዚያ አስወገደ። እነዚህም ናታን ሜሌክ በተባለ በአንድ ሹም ቤት አጠገብ በአደባባዩ ላይ ነበሩ። ኢዮስያስም ለፀሓይ አምልኮ የተሰጡትን ሠረገሎች አቃጠለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የይሁዳ ነገሥታት ለፀሐይ አምልኮ መድበዋቸው የነበሩትን ፈረሶች ሁሉ አስወገደ፤ ለዚሁ አምልኮ የሚያገለግሉ የነበሩትን ሠረገሎች አቃጠለ፤ እነዚህ ሁሉ ቀደም ሲል ታላቁ ባለ ሥልጣን ናታን ሜሌክ በሚኖርባቸው ክፍሎች አጠገብና በቤተ መቅደሱ አደባባይ ቅጽር በር አጠገብ ይገኙ ነበር፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የይሁዳ ነገሥታት ለፀሐይ አምልኮ መድበዋቸው የነበሩትን ፈረሶች ሁሉ አስወገደ፤ ለዚሁ አምልኮ የሚያገለግሉ የነበሩትን ሠረገሎች አቃጠለ፤ እነዚህ ሁሉ ቀደም ሲል ታላቁ ባለሥልጣን ናታን ሜሌክ በሚኖርባቸው ክፍሎች አጠገብና በቤተ መቅደሱ አደባባይ ቅጽር በር አጠገብ ይገኙ ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መግ​ቢያ አጠ​ገብ በከ​ተ​ማው አቅ​ራ​ቢያ በነ​በ​ረው በን​ጉሡ ጃን​ደ​ረባ በና​ታን መኖ​ሪያ አጠ​ገብ ለፀ​ሐይ የሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ፈረ​ሶች አቃ​ጠለ፤ የፀ​ሐ​ይ​ንም ሰረ​ገ​ሎች በእ​ሳት አቃ​ጠለ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 23:11
8 交叉引用  

የይሁዳ ነገሥታትም በይሁዳ ከተሞች በነበሩት በኮረብታው መገጃዎች በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ መስገጃዎች ያጥኑ ዘንድ ያኖሩአቸውን የጣዖቱን ካህናት፥ ለበኣልና ለፀሐይ ለጨረቃና ለከዋክብት ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ያጥኑ የነበሩትንም አስወገደ።


በምዕራብ በኩል በፈርባር መንገድ ላይ አራት፥ በፈርባርም አጠገብ ሁለት ነበሩ።


ከይሁዳም ከተሞች ሁሉ የኮረብታውን መስገጃዎችና የፀሐይ ምስሎችን አስወገደ፤ መንግሥቱም በእርሱ ሥር በሰላም ተቀመጠች።


የበኣሊምንም መሠዊያዎች በፊቱ አፈረሱ፤ በላዩም የነበሩትን የፀሐዩን ምስሎች የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጠ፤ የተቀረጹትንና ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎች ሰባበረ፤ አደቀቃቸውም፤ ይሠዉላቸው በነበሩት ሰዎች መቃብርም ላይ በተናቸው።


ፀሐይ ሲበራ ጨረቃም በክብር ስትሄድ አይቼ፥


ወደ ውጭውም አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆም፥ በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ዕቃ ቤቶችና ወለል ነበሩ፥ በወለሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።


ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆም፥ በእግዚአብሔር መቅደስ መግቢያ ፊት በወለሉና በመሠዊያው መካከል ሃያ አምስት የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ ጀርባቸውም ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ነበረ፥ እነርሱም ወደ ምሥራቅ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።


ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አንሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕዛብ ሁሉ የሰጣቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንና የሰማይን ሠራዊት ሁሉ ባየህ ጊዜ፥ ሰግደህላቸው አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ።


跟着我们:

广告


广告