Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 22:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እነርሱም ለድንቅና ለመርገም እንዲሆኑ በዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ የተናገርሁትን ሰምተህ በእግዚአብሔር ፊት ተዋርደሃልና፥ ልብስህን ቀድደሃልና፥ በፊቴም አልቅሰሃልና እኔ ደግሞ ሰምቼሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ለርግማንና ለጥፋት የተዳረጉ ስለ መሆናቸው በዚህ ስፍራና በሕዝቡ ላይ የተናገርኩትን በሰማህ ጊዜ ልብህ ስለ ተነካና በእግዚአብሔር ፊት ራስህን ስላዋረድህ፣ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ ስላለቀስህ እኔም ሰምቼሃለሁ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ይህችን ቦታና ሕዝብዋን የተረገሙና ባድማ እንደማደርግ የተናገርኩትን ቃል በሰማህ ጊዜ ልብህ ተነክቶ ራስህን በማዋረድ፥ ልብስህን በመቅደድና በፊቴም በማልቀስህ ጸሎትህን ሰምቼአለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ይህችን ቦታና ሕዝብዋን የተረገሙና ባድማ እንደማደርግ የተናገርኩትን ቃል በሰማህ ጊዜ ልብህ ተነክቶ ራስህን በማዋረድ፥ ልብስህን በመቅደድና በፊቴም በማልቀስህ ጸሎትህን ሰምቼአለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ልብ​ህን አላ​ደ​ነ​ደ​ን​ህ​ምና፥ እነ​ር​ሱም ለጥ​ፋ​ትና ለመ​ር​ገም እን​ዲ​ሆኑ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሰም​ተህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህን ቀድ​ደ​ሃ​ልና፥ በፊ​ቴም አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制




2 ነገሥት 22:19
44 交叉引用  

እነዚህም በእነዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰባተኛውም ቀን ተጋጠሙ፥ የእስራኤልም ልጆች ከሶርያውያን በአንድ ቀን መቶ ሺህ እግረኛ ገደሉ።


የአሞጽም ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ወደ ሕዝቅያስ ላከ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ የለመንኽውን ሰምቻለሁ።


“ተመልሰህ የሕዝቤን አለቃ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው ‘የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፥ እፈውስሃለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወጣለህ።


ንጉሡም የሕጉን መጽሐፍ ቃል በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ።


ሕዝቅያስም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኵራት ሰውነቱን አዋረደ፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ በሕዝቅያስ ዘመን አልመጣባቸውም።


በተጨነቀም ጊዜ አምላኩን እግዚአብሔርን ፈለገ፤ በአባቶቹም አምላክ ፊት ሰውነቱን እጅግ አዋረደ፤


ደግሞም ጸሎቱ፥ እግዚአብሔርም እንደ ተለመነው፥ ኃጢያቱና መተላለፉ ሁሉ፥ ራሱንም ሳያዋርድ የኮረብታው መስገጃዎችን የሰራበት የማምለኪያ ዐፀዱንና የተቀረጹትንም ምስሎች የተከለበት ስፍራ፥ እነሆ፥ በባለ ራእዩ ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።


አባቱም ምናሴ ሰውነቱን እንዳዋረደ በእግዚአብሔር ፊት ሰውነቱን አላዋረደም፤ ነገር ግን አሞን መተላለፉን እጅግ አበዛ።


በፊቴም ራስህን አዋርደሃልና፥ በዚህም ስፍራና በሚኖሩበት ላይ ቃሌን በሰማህ ጊዜ ራስህን አዋርደሃልና፥ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ አልቅሰሃልና እኔ ደግሞ ሰምቼሃለሁ’ ይላል እግዚአብሔር።


ዕዝራም እያለቀሰና በእግዚአብሔር ቤት ፊት እየወደቀ በጸለየና በተናዘዘ ጊዜ ከእስራኤል ዘንድ የወንድና የሴት የሕፃናትም እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፤ ሕዝቡም እጅግ አለቀሱ።


ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፤


ሐቴርሰታ ነህምያም ጸሐፊውም ካህኑ ዕዝራ ሕዝቡንም የሚያስተምሩ ሌዋውያን ሕዝቡን ሁሉ፦ ዛሬ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ቀን ነው፥ አታልቅሱ እንባም አታፍስሱ አሉአቸው፥ ሕዝቡ ሁሉ የሕጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለቅሱ ነበርና።


ሙሴም አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ አሉትም፤ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በፊቴ ለመዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ያገለግሉኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።


እናንተ ከጽድቅ የራቃችሁ እልከኞች፥ ስሙኝ፥


ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።


እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር፥ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።


በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ የጠሉአችሁ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ ወንድሞቻችሁ፦ ደስታችሁን እናይ ዘንድ እግዚአብሔር ይክበር ብለዋል፥ ነገር ግን ያፍራሉ።


ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፥ የእግዚአብሔርም መንጋ ተማርኮአልና ዓይኔ ታነባለች፥ እንባንም ታፈስሳለች።


እንደዚህም ብለህ ትነግራቸዋለህ፦ የወገኔ ልጅ ድንግሊቱ በታላቅ ስብራትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰብራለችና ዓይኖቼ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ።


ይህን ቤት እንደ ሴሎ አደርገዋለሁ፥ ይህችንም ከተማ ለምድር አሕዛብ ሁሉ እርግማን አደርጋታለሁ።


ሚክያስም ባሮክ በሕዝቡ ጆሮ በመጽሐፉ ባነበበ ጊዜ የሰማውን ቃል ሁሉ ነገራቸው።


ንጉሡም ይህንም ቃል ሁሉ የሰሙ ባሪያዎቹ ሁሉ አልፈሩም ልብሳቸውንም አልቀደዱም።


እግዚአብሔርም ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኵሰት ይታገሥ ዘንድ አልቻለም፥ ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ መደነቂያም መረገሚያም ሆናለች ዛሬም እንደ ሆነ የሚኖርባት የለም።


ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!


እግዚአብሔርም፦ በከተማይቱ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኵሰት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክት ጻፍ አለው።


ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?


እነሆም፥ ከእስራኤል ልጆች አንዱ መጥቶ በሙሴና በእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ፊት ምድያማዊቱን አንዲቱን ሴት ወደ ወንድሞቹ አመጣት፤ እነርሱም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያለቅሱ ነበር።


ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ አለቀሰላት፥


ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው መቃጠልም እንደ ሆነባት፥ እንዳትዘራም እንዳታበቅልም፥ ማናቸውም ሣርና ልምላሜም እንዳይወጣባት፥ እግዚአብሔር በቁጣውና በመዓቱ እንደ ገለባበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ እንደ አዳማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥


የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ ወጥተው ወደ ቤቴል መጡ፥ አለቀሱም፥ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፥ በዚያም ቀን እስከ ማታ ድረስ ጾሙ፥ በእግዚአብሔር ፊት የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕት አቀረቡ።


ከዚያም በኋላ እንዲህ ሆነ፥ የሳኦልን የልብሱን ዘርፍ ስለቆረጠ የዳዊት ልብ በኅዘን ተመታ።


跟着我们:

广告


广告