Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 20:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 “ተመልሰህ የሕዝቤን አለቃ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው ‘የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፥ እፈውስሃለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወጣለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ተመለስና የሕዝቤን አለቃ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፤ ‘የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፤ እፈውስሃለሁ። ከዛሬ ሦስት ቀን በኋላ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “ሕዝቤን ወደሚመራው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ተመልሰህ በመግባት እንዲህ በለው፦ ‘እኔ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም ተመልክቻለሁ፤ እኔ እፈውስሃለሁ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ሕዝቤን ወደሚመራው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ተመልሰህ በመግባት እንዲህ በለው፦ ‘እኔ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም ተመልክቻለሁ፤ እኔ እፈውስሃለሁ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “ተመ​ል​ሰህ የሕ​ዝ​ቤን ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ በለው፦ የአ​ባ​ትህ የዳ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጸሎ​ት​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፥ እን​ባ​ህ​ንም አይ​ቻ​ለሁ፤ እነሆ፥ እኔ እፈ​ው​ስ​ሃ​ለሁ፤ እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ትወ​ጣ​ለህ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 20:5
44 交叉引用  

አስቀድሞ ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን የምታወጣና የምታገባ አንተ ነበርህ፥ እግዚአብሔርም፦ አንተ ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፥ በእስራኤልም ላይ አለቃ ትሆናለህ ብሎህ ነበር አሉት።


እግዚአብሔርም አለው “በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ፤ ለዘላለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ፤ ዐይኖቼና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ።


የአሞጽም ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ወደ ሕዝቅያስ ላከ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ የለመንኽውን ሰምቻለሁ።


ኢሳይያስም ወደ መካከለኛው ከተማ አደባባይ ሳይደርስ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት


እነርሱም ለድንቅና ለመርገም እንዲሆኑ በዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ የተናገርሁትን ሰምተህ በእግዚአብሔር ፊት ተዋርደሃልና፥ ልብስህን ቀድደሃልና፥ በፊቴም አልቅሰሃልና እኔ ደግሞ ሰምቼሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።


እነሆም፥ እግዚአብሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለከቱንም የሚነፉ ካህናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእናንተም ላይ ይጮኸሉ። የእስራኤ ልጆች ሆይ፥ አይበጃችሁምና ከአባቶቻሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር አትዋጉ።”


በነገሠም በስምንተኛው ዓመት ገና ብላቴና ሳለ የአባቱን የዳዊትን አምላክ ይፈልግ ጀመር፤ በአሥራ ሁለተኛውም ዓመት ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከኮረብታው መስገጃዎችና ከማምለኪያ ዐፀዶቹ፥ ከተቀረጹትና ቀልጠው ከተሰሩት ምስሎች ያነጻ ጀመር።


እርሱም፦ አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም የሚበጀውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና አለ።


እግዚአብሔርም አለ፦ “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፤ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ።


አሁንም እነሆ የእስራኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ ወጣ፤ ግብፃውያንም የሚያደርጉባቸውን ግፍ ደግሞ አየሁ።


እግዚአብሔርም ግብጽን ይመታታል፥ ይመታታል ይፈውሳታልም፥ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ እርሱም ይለመናቸዋል ይፈውሳቸውማል።


ሕዝቅያስም፦ ወደ እግዚአብሔር ቤት እወጣ ዘንድ ምልክቱ ምንድር ነው? ብሎ ነበር።


ሂድ፥ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፥ እነሆ፥ በዕድሜህ ላይ አሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ።


ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፥ ስሙ ሰውነታችሁም በሕይወት ትኖራለች፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘላለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።


መልአኩም እንዲህ አለው፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።


እንዲህ ሲል፦ ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስ አገኘውና፦ እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው።


አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ 2 ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤ 2 እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ፤ 2 እኔ እመታለሁ፥ እፈውስማለሁ፤ 2 ከእጄም የሚያድን የለም።


ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ሲያመጣ የመዳናቸውን ራስ በመከራ ይፈጽም ዘንድ፥ ከእርሱ የተነሣ ሁሉ በእርሱም ሁሉ ለሆነ፥ ለእርሱ ተገብቶታልና።


በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፥ ወደ ሕይወትም ውኃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል።


ሳሙኤልም የዘይቱን ብርሌ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፥ ሳመውም፥ እንዲህም አለው፦ በርስቱ ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶሃል፥ የእግዚአብሔርንም ሕዝብ ትገዛለህ፥ በዙሪያውም ካሉ ጠላቶቻቸው እጅ ታድናቸዋለህ።


ነገ በዚህች ሰዓት ከብንያም አገር አንድ ሰው እሰድድልሃለሁ፥ ልቅሶአቸው ወደ እኔ የደረስ ሕዝቤን ተመልክቻለሁና ለሕዝቤ ለእስራኤል አለቃ ይሆን ዘንድ ትቀባዋለህ፥ ከፍልስጥኤማውያን እጅ ሕዝቤን ያድናል።


跟着我们:

广告


广告