Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 20:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሕዝቅያስም ኢሳይያስን “የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው፤” አለው። ደግሞም “በዘመኔ ሰላምና እውነት የሆነ እንደ ሆነ መልካም አይደለምን?” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፣ “የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው” ሲል መለሰ፤ “እኔ እስካለሁ ድረስ ሰላምና ጸጥታ ከተገኘ ምን ይገድደኛል?” ብሎ ዐስቦ ነበርና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ንጉሥ ሕዝቅያስም በተለይ በእርሱ ዘመን በሰላም የመኖር ዋስትና እንዳለ ስለ ተረዳ “ከእግዚአብሔር ተልከህ የተናገርከኝ ቃል መልካም ነው” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ንጉሥ ሕዝቅያስም በተለይ በእርሱ ዘመን በሰላም የመኖር ዋስትና እንዳለ ስለ ተረዳ “ከእግዚአብሔር ተልከህ የተናገርከኝ ቃል መልካም ነው” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው ቃል መል​ካም ነው። ደግ​ሞም በዘ​መኔ ሰላም ይሁን” አለው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 20:19
15 交叉引用  

ነገር ግን ከልጅህ እጅ እቀድደዋለሁ እንጂ ስለ አባትህ ስለ ዳዊት ይህን በዘመንህ አላደርግም።


ሳሚም ንጉሡን “ነገሩ መልካም ነው፤ ጌታዬ ንጉሥ እንደ ተናገረ ባሪያህ እንዲሁ ያደርጋል፤” አለው፤ ሳሚም በኢየሩሳሌም ብዙ ቀን ተቀመጠ።


የቀረውም የሕዝቅያስ ነገር፥ ጭከናውም ሁሉ፥ ኵሬውንና መስኖውንም እንደ ሠራ፥ ውሃውንም ወደ ከተማይቱ እንዳመጣ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?


ስለዚህም ደግሞ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፤ በሰላምም ወደ መቃብርህ ትሰበሰባለህ፤ በዚህም ስፍራ ላይ የማመጣውን ክፉ ነገር ዐይኖችህ አያዩም።’” ይህንም ለንጉሡ አወሩለት።


ደብዳቤዎቹንም በአርጤክስስ መንግሥት በመቶ ሀያ ሰባቱ አገሮች ወዳሉ አይሁድ ሁሉ በሰላምና በእውነት ቃል ላኩ።


እንዲህም አለ፦ ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፥ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ነሣ፥ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን።


እነሆ፥ ፈውስንና መድኃኒትን አመጣላታለሁ፥ እፈውሳቸውማለሁ፥ የሰላምንና የእውነትን ብዛት እገልጥላቸዋለሁ።


ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፥ ርኅራኄው አያልቅምና።


ሕያው ሰው የሚያጉረመርም፥ ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት የሚያጕረመርም ስለ ምንድር ነው?


ሙሴም አሮንን፦ እግዚአብሔር፦ ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀደሳለሁ፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ ብሎ የተናገረው ይህ ነው አለው፤ አሮንም ዝም አለ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፥ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።


መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤


ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።


ሳሙኤልም ነገሩን ሁሉ ነገረው፥ አንዳችም አልሸሸገውም። ዔሊም፦ እርሱ እግዚአብሔር ነው፥ ደስ ያሰኘውን ያድርግ አለ።


跟着我们:

广告


广告