Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በኢያሪኮም የነበሩ የነቢያት ልጆች ወደ ኤልሳዕ ቀርበው “እግዚአብሔር ጌታህን ከራስህ ላይ ዛሬ እንዲወስደው አውቀሃልን?” አሉት። እርሱም “አዎን፥ አውቄአለሁ፤ ዝም በሉ፤” ብሎ መለሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በኢያሪኮ የነበሩትም የነቢያት ማኅበር ወደ ኤልሳዕ ወጥተው፣ “ለመሆኑ እግዚአብሔር፣ ጌታህን ኤልያስን ዛሬ ከአንተ ነጥሎ እንደሚወስደው ዐውቀሃልን?” አሉት። እርሱም፣ “አዎን ዐውቄአለሁ፤ እናንተ ግን ዝም በሉ” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በዚያም የሚኖሩ የነቢያት ጉባኤ ወደ ኤልሳዕ ሄደው፥ “እግዚአብሔር ዛሬ ጌታህን ከአንተ ለይቶ እንደሚወስደው ታውቃለህን?” ሲሉ ጠየቁት። ኤልሳዕም “አዎ ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ዝም በሉ” ሲል መለሰላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በዚያም የሚኖሩ የነቢያት ጉባኤ ወደ ኤልሳዕ ሄደው፥ “እግዚአብሔር ዛሬ ጌታህን ከአንተ ለይቶ እንደሚወስደው ታውቃለህን?” ሲሉ ጠየቁት። ኤልሳዕም “አዎ ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ዝም በሉ” ሲል መለሰላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ወደ ኢያ​ሪ​ኮም ደረሱ፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም የነ​በሩ የነ​ቢ​ያት ልጆች ወደ ኤል​ሳዕ ቀር​በው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጌታ​ህን ከራ​ስህ ላይ ዛሬ እን​ዲ​ወ​ስ​ደው ዐው​ቀ​ሃ​ልን?” አሉት። እር​ሱም፥ “አዎን፥ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ ዝም በሉ” አላ​ቸው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 2:5
18 交叉引用  

አባቱም እንቢ አለ እንዲህ ሲል፦ አወቅሁ ልጄ ሆይ አወቅሁ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆናል ታላቅም ይሆናል ነገር ግን ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል ዘሩም የአሕዛብ ሙላት ይሆናል።


በቤቴልም የነበሩ የነቢያት ልጆች ወደ ኤልሳዕ ወጥተው “እግዚአብሔር ጌታህን ከራስህ ላይ ዛሬ እንዲወስደው አውቀሃልን?” አሉት። እርሱም “አዎን፥ አውቄአለሁ፤ ዝም በሉ፤” አላቸው።


ከነቢያትም ወገን ሚስቶች አንዲት ሴት “ባሌ ባሪያህ ሞቶአል፤ ባሪያህም እግዚአብሔርን ይፈራ እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ፤ ባለ ዕዳ ሁለት ልጆቼን ባሪያዎች አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቶአል፤” ብላ ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።


እርሱም “ደኅና ነው፤ ‘አሁን ከነቢያት ወገን የሆኑት ሁለት ጕልማሶች ከተራራማው ከኤፍሬም አገር ወደ እኔ መጥተዋል፤ አንድ መክሊት ብርና ሁለት መለወጫ ልብስ ትሰጣቸው ዘንድ እለምንሃለሁ፤’ ብሎ ጌታዬ ላከኝ፤” አለ።


የነቢያት ልጆች ኤልሳዕን “እነሆ፥ በፊትህ የምንቀመጥበት ስፍራ ጠብቦናል።


ነቢዩም ኤልሳዕ ከነቢያት ልጆች አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለው “ወገብህን ታጥቀህ ይህን የዘይት ማሰሮ በእጅህ ያዝ፤ ወደ ሬማት ዘገለዓድም ሂድ።


ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋትም ጊዜ አለው፥ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፥


ደሴቶች ሆይ፥ በፊቴ ዝም በሉ፥ አሕዛብም ኃይላቸውን ያድሱ፥ ይቅረቡም በዚያን ጊዜም ይናገሩ፥ ለፍርድ በአንድነት እንቅረብ።


አሞጽም መልሶ አሜስያስን አለው፦ እኔ ላም ጠባቂና ወርካ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፥


እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፥ ምድርም ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል።


ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።


ደግሞም፦ “የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል” አሉአቸው።


ጳውሎስ ግን እንዲህ አለ፦ “ክቡር ፊስጦስ ሆይ፥ የእውነትንና የአምሮን ነገር እናገራለሁ እንጂ እብደትስ የለብኝም።


ከዚያም በኋላ የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህ፥ ወደዚያም ወደ ከተማይቱ በደረስህ ጊዜ፥ በገናና ከበሮ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩ ከኮረብታው መስገጃ የሚወርዱ የነቢያት ጉባኤ ያገኙሃል።


跟着我们:

广告


广告