Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 2:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ውሃውም ወዳለበት ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለበትና “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ይህን ውሃ ፈውሼዋለሁ፤ ከዚህም በኋላ ሞትና ጭንገፋ አይሆንበትም፤’” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከዚያም ወደ ውሃው ምንጭ ሄዶ ጨው ጣለበትና “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ይህን ውሃ ፈውሼዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ለሞት ምክንያት አይሆንም፤ ምድሪቱንም ፍሬ እንዳትሰጥ አያደርጋትም’ አለ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እርሱም ወደ ምንጩ ሄዶ ጨውን በውሃው ውስጥ በመጨመር፥ “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው ‘እኔ ይህን ውሃ በመፈወስ ንጹሕ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ የሞትና የምርት አልባነት ምክንያት አይሆንም’” ሲል ተናገረ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እርሱም ወደ ምንጩ ሄዶ ጨውን በውሃው ውስጥ በመጨመር፥ “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው ‘እኔ ይህን ውሃ በመፈወስ ንጹሕ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ የሞትና የምርት አልባነት ምክንያት አይሆንም’ ” ሲል ተናገረ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ውኃው ወዳ​ለ​በ​ትም ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለ​በ​ትና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህን ውኃ ፈው​ሼ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ህም በኋላ የሚ​ሞት፥ የሚ​መ​ክ​ንም አይ​ኖ​ርም” አለ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 2:21
14 交叉引用  

እርሱም “አዲስ ማሰሮ አምጡልኝ፤ ጨውም ጨምሩበት፤” አለ፤ ያንንም አመጡለት።


ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ነገር ውሃው እስከ ዛሬ ድረስ ተፈውሶአል።


እርሱም “ዱቄት አምጡልኝ፤” አለ፤ በምንቸቱም ውስጥ ጥሎ “ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ቅዱ፤” አለ። በምንቸቱም ውስጥ ክፉ ነገር አልተገኘም።


የእግዚአብሔርም ሰው “የወደቀው ወዴት ነው?” አለ ስፍራውንም አሳየው፤ እንጨትም ቆርጦ በዚያ ጣለው፤ ብረቱም ተንሳፈፈ።


የምታቀርበውን የእህል ቍርባን ሁሉ በጨው ታጣፍጠዋለህ፤ የአምላክህንም ቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቍርባንህ አታጐድልም፤ በቍርባንህ ሁሉ ላይ ጨው ታቀርባለህ።


ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።


ጨው መልካም ነው፤ ጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ? በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።


ይህን ብሎ ወደ መሬት እንትፍ አለ በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዕውሩን ዓይኖች ቀባና፦


እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።


跟着我们:

广告


广告