Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 2:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ኤልያስም ኤልሳዕን “እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ልኮኛልና በዚህ ቆይ፤” አለው። ኤልሳዕም “ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ አልለይህም፤” አለ። ወደ ቤቴልም ወረዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ኤልያስም ኤልሳዕን፣ “እግዚአብሔር እኔን ወደ ቤቴል ልኮኛልና አንተ በዚሁ ቈይ” አለው። ኤልሳዕ ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን፣ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ ከአንተ አልለይም” አለው። ስለዚህ ዐብረው ወደ ቤቴል ወረዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በመንገድም ሳሉ ኤልያስ ኤልሳዕን “እነሆ፥ አንተ በዚህ ቆይ፤ እኔ ወደ ቤትኤል እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ ከቶ ከአንተ አልለይም” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ወደ ቤትኤል ሄዱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በመንገድም ሳሉ ኤልያስ ኤልሳዕን “እነሆ፥ አንተ በዚህ ቈይ፤ እኔ ወደ ቤትኤል እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል” አለው። ኤልሳዕ ግን “እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ ከቶ ከአንተ አልለይም” ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ወደ ቤትኤል ሄዱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ኤል​ያ​ስም ኤል​ሳ​ዕን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ቤቴል ልኮ​ኛ​ልና በዚሁ ቈይ” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም አል​ለ​ይ​ህም” አለው። ወደ ቤቴ​ልም ደረሱ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 2:2
17 交叉引用  

ያዕቆብም ይንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው አስቀድሞ ግን የዚያች ከተማ ስም ሎዛ ነበረ።


ንጉሡም ተማከረ፤ ሁለትም የወርቅ ጥጆች አድርጎ “እስራኤል ሆይ! ወደ ኢየሩሳሌም ትወጡ ዘንድ ይበዛባችኋል፤ ከግብጽ ምድር ያወጡህን አማልክቶችህን እይ!” አላቸው።


አንዱን በቤቴል፥ ሁለተኛውንም በዳን አኖረ።


በስምንተኛውም ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን በልቡ ባሰበው ቀን በቤቴል በሠራው መሠዊያ ላይ ሠዋ፤ ለእስራኤልም ልጆች በዓል አደረገላቸው፤ በመሠዊያውም ሠዋ፤ ዕጣንም ዐጠነ።


ከዚያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድም ሲወጣ ብላቴኖች ከከተማይቱ ወጥተው “አንተ መላጣ፥ ውጣ! አንተ መላጣ፥ ውጣ!” ብለው አፌዙበት።


ኤልያስም “ኤልሳዕ ሆይ! እግዚአብሔር ወደ ኢያሪኮ ልኮኛልና እባክህ፥ በዚህ ቆይ፤” አለው። እርሱም “ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ አልለይህም” አለ። ወደ ኢያሪኮም መጡ።


ኤልያስም “እግዚአብሔር ወደ ዮርዳኖስ ልኮኛልና እባክህ፥ በዚህ ቆይ፤” አለው። እርሱም “ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ አልለይህም፤” አለ። ሁለቱም ሄዱ።


የሕፃኑም እናት “ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ! አልተውህም፤” አለች፤ ተነሥቶም ተከተላት።


ሕያው እግዚአብሔርን! ብለህም በእውነትና በቅንነት በጽድቅም ብትምል፥ አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ በእርሱም ይመካሉ።


ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።


እርስዋም አለች፦ ጌታዬ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ጌታ ሆይ፥ ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ በዚህ በአንተ ዘንድ ቆማ የነበረች ሴት እኔ ነኝ።


ሳኦልም ዳዊትን ወደ ፍልስጥኤማዊው ሲወጣ ባየው ጊዜ ለሠራዊቱ አለቃ ለአበኔር፦ አበኔር ሆይ፥ ይህ ብላቴና የማን ልጅ ነው? አለው። አበኔርም፦ ንጉሥ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፥ አላውቅም አለ።


አሁንም፥ ጌታዬ ሆይ፥ ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ! ወደ ደም እንዳትገባ፥ እጅህም ራስህን እንዳታድን የከለከለህ እግዚአብሔር ነው፥ አሁንም ጠላቶችህና በጌታዬ ላይ ክፉ የሚሹ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ።


跟着我们:

广告


广告