Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 2:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የከተማይቱም ሰዎች ኤልሳዕን “እነሆ፥ ጌታችን እንደምታይ የዚች ከተማ ኑሮ መልካም ነው፤ ውሃው ግን ክፉ ነው፤ ምድሪቱም ፍሬዋን ትጨነግፋለች፤” አሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የከተማዪቱም ሰዎች ኤልሳዕን፣ “እነሆ ጌታችን፤ እንደምታያት ይህች ከተማ ለኑሮ የተመቸች ናት፤ ይሁን እንጂ ውሃው መጥፎ ሲሆን ምድሪቱም ፍሬ የማትሰጥ ናት” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ጥቂት ሰዎች ከኢያሪኮ ወደ ኤልሳዕ መጥተው “ጌታችን አንተ እንደምታውቀው ይህች ምድር መልካም ናት፤ ውሃው ግን መጥፎ በመሆኑ ምድሪቱ ምርት አትሰጥም” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ጥቂት ሰዎች ከኢያሪኮ ወደ ኤልሳዕ መጥተው “ጌታችን አንተ እንደምታውቀው ይህች ምድር መልካም ናት፤ ውሃው ግን መጥፎ በመሆኑ ምድሪቱ ምርት አትሰጥም” አሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሰዎች ኤል​ሳ​ዕን፥ “እነሆ፥ ጌታ​ችን እን​ደ​ም​ታይ የዚች ከተማ ኑሮ መል​ካም ነው፤ ውኃው ግን ክፉ ነው፤ ሴቶ​ችም ሲጠ​ጡት ይመ​ክ​ናሉ፥” አሉት።

参见章节 复制




2 ነገሥት 2:19
16 交叉引用  

በእርሱም ዘመን የቤቴል ሰው አኪኤል ኢያሪኮን ሠራ፤ በነዌም ልጅ በኢያሱ አማካይነት እንደ ተነገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል፥ በበኵር ልጁ በአቢሮን መሠረትዋን አደረገ፤ በታናሹ ልጁም በሠጉብ በሮችዋን አቆመ።


ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ፥ መቶውን የእግዚአብሔር ነቢያት ወስጄ፥ አምሳ አምሳውንም በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ፥ እንጀራና ውሃ የመገብኋቸው፥ ይህ ያደርግሁት ነገር በውኑ ለጌታዬ አልታወቀህምን?


አብድዩም በመንገድ ሲሄድ፥ እነሆ፥ ኤልያስ ተገናኘው፤ አብድዩም አወቀው፤ በግምባሩም ተደፍቶ “ጌታዬ ሆይ! ኤልያስ አንተ ነህን?” አለ።


በኢያሪኮም ተቀምጦ ሳለ ወደ እርሱ ተመለሱ፤ እርሱም “አትሂዱ አላልኋችሁምን?” አላቸው።


እርሱም “አዲስ ማሰሮ አምጡልኝ፤ ጨውም ጨምሩበት፤” አለ፤ ያንንም አመጡለት።


ወደ ማራም በመጡ ጊዜ የማራ ውኃ መራራ ነበረና ሊጠጡ አልቻሉም፤ ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም ማራ ተብሎ ተጠራ።


በምድርህም መካን ወይም የምትጨነግፍ አትሆንም፤ የዘመንህን ቍጥር እሞላለሁ።


እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “አሮንን፥ ‘በትርህን ውሰድ፤ ደምም እንዲሆኑ በግብፅ ውኆች በወንዞቻቸውም በመስኖቻቸውም በኩሬዎቻቸውም በውኃ ማከማቻዎቻቸውም ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ’ በለው፤ በግብፅም አገር ሁሉ በእንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ይሆናል።”


አቤቱ፥ ስጣቸው፥ ምን ትሰጣቸዋለህ? የሚጨነግፍን ማኅፀን የደረቀውንም ጡት ስጣቸው።


አሮንም ሙሴን፦ ጌታዬ ሆይ፥ ስንፍና አድርገናልና፥ በድለንማልና እባክህ፥ ኃጢአት አታድርግብን።


እግዚአብሔርም እርስዋን ይሰጥህ ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው በምድርህ ላይ፥ በሆድህ ፍሬ፥ በከብትህ ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ እግዚአብሔር በጎነቱን በላይህ ያበዛል።


በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።


ከተማይቱም በእርስዋም ያለው ሁሉ ለእግዚአብሔር እርም ይሆናሉ፥ የላክናቸውን መልክተኞች ስለ ሸሸገች ጋለሞታይቱ ረዓብ ከእርስዋም ጋር በቤትዋ ውስጥ ያሉ ሁሉ ብቻ በሕይወት ይኖራሉ።


በዚያን ጊዜም ኢያሱ፦ ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ርጉም ይሁን፥ መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይጥፋ፥ በርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይጥፋ ብሎ ማለ።


跟着我们:

广告


广告