Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 19:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 “‘እኔ ጥንቱን እንደ ሠራሁት፥ ቀድሞውንም እንዳደረግሁት አልሰማህምን? አሁንም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር እስኪሆኑ ድረስ እንድታፈርስ አደረግሁህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “ ‘ይህን ቀድሞ እንደ ወሰንሁት፣ አልሰማህምን? ጥንትም እንዳቀድሁት፣ አሁን ግን እንዲፈጸም አደረግሁት፤ ይህም የተመሸጉትን ከተሞች፣ አንተ የድንጋይ ክምር ማድረግህ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ሰናክሬም ሆይ! አስተውል፤ ጥንቱኑ እኔ እንደ ወሰንኩት፥ በቀድሞ ዘመን እንደ ዐቀድኩትና አሁን በሥራ ላይ ባዋልኩት መሠረት የተጠናከሩ ከተሞችን ወደ ፍርስራሽ ክምርነት እንድትለውጥ ያደረግኹህ እኔ መሆኔን አልሰማህምን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ሰናክሬም ሆይ! አስተውል፤ ጥንቱኑ እኔ እንደ ወሰንኩት፥ በቀድሞ ዘመን እንደ ዐቀድኩትና አሁን በሥራ ላይ ባዋልኩት መሠረት የተጠናከሩ ከተሞችን ወደ ፍርስራሽ ክምርነት እንድትለውጥ ያደረግኹህ እኔ መሆኔን አልሰማህምን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “እኔ ጥን​ቱን እንደ ሠራ​ሁት፥ ቀድ​ሞ​ው​ንም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? አሁ​ንም የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች የፍ​ር​ስ​ራሽ ክምር እስ​ኪ​ሆኑ ድረስ እን​ድ​ታ​ፈ​ርስ አደ​ረ​ግ​ሁህ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 19:25
11 交叉引用  

በውኑ መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይመካልን? ወይስ መጋዝ በሚስበው ሰው ላይ ይጓደዳልን? ይህስ፥ በትር የሚያነሳውን እንደ መነቅነቅ ዘንግም እንጨት ያይደለውን እንደ ማንሳት ያህል ነው።


ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ፥ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ፥ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።


እናንተ ሰማያት ከላይ አንጠባጥቡ ደመናትም ጽድቅን ያዝንቡ፥ ምድርም ትከፈት መድኃኒትንም ታብቅል፥ ጽድቅም በአንድነት ይብቀል፥ እኔ እግዚአብሔር ፈጥሬዋለሁ።


እነሆ፥ ፍሙን በወናፍ የሚያናፋ ለሥራውም መሣሪያ የሚያወጣ ብረት ሠሪን እኔ ፈጥሬአለሁ፥ የሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ ፈጥሬአለሁ።


ስለዚህ ሰማርያን በሜዳ እንደሚገኝ የድንጋይ ክምር፥ ወይን እንደሚተከልበትም ስፍራ አደርጋታለሁ፥ ድንጋዮችዋንም ወደ ሸለቆ እወረውራለሁ፥ መሠረቶችዋንም እገልጣለሁ።


跟着我们:

广告


广告