Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 18:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ፤ የሚሄድበትም መንገድ ተከናወነለት፤ በአሦርም ንጉሥ ላይ ዐመፀ፤ አልገበረለትም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ ስለ ነበር የሚያደርገው ሁሉ ተከናወነለት። በአሦር ንጉሥ ላይ ዐመፀ፤ ግብር መገበሩንም ተወ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለዚህም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ሆኖ ስለሚረዳው የሚሠራው ሁሉ በተቃና ሁኔታ ይከናወንለት ነበር፤ ሕዝቅያስ በአሦር ንጉሠ ነገሥት ላይ ዐምፆ ለእርሱ መገዛትን አሻፈረኝ አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ስለዚህም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ሆኖ ስለሚረዳው የሚሠራው ሁሉ በተቃና ሁኔታ ይከናወንለት ነበር፤ ሕዝቅያስ በአሦር ንጉሠ ነገሥት ላይ ዐምፆ ለእርሱ መገዛትን አሻፈረኝ አለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በሚ​ሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ በአ​ሦ​ርም ንጉሥ ላይ ዐመፀ፤ አል​ተ​ገ​ዛ​ለ​ት​ምም።

参见章节 复制




2 ነገሥት 18:7
23 交叉引用  

በዚያም ዘመን አቢሜሌክ ከሙሽራው ወዳጅ ከአኮዘትና ከሠራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር አብርሃምን አለው፤ በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤


በኤዶምያስ ሁሉ ጭፍሮች አኖረ፥ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ እግዚአብሔርም ዳዊት በሚሄድበት ሁሉ ድልን ሰጠው።


ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ ጭፍሮች አኖረ፥ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ ግብርም አመጡለት፥ እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።


አካዝም “እኔ ባሪያህና ልጅህ ነኝ፤ መጥተህ ከተነሡብን ከሶርያ ንጉሥና ከእስራኤል ንጉሥ እጅ አድነኝ፤” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ቴልጌልቴልፌልሶር መልእክተኞችን ላከ።


የአሦርም ንጉሥ ስልምናሶር በእርሱ ላይ ወጣ፤ ሆሴዕም ተገዛለት፤ ግብርም አመጣለት።


የይሁዳም ንጉሥ ሕዝቅያስ “በድያለሁ፤ ከእኔ ተመለስ፤ የምትጭንብኝን ሁሉ እሸከማለሁ፤” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ለኪሶ ላከ። የአሦርም ንጉሥ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ላይ ሦስት መቶ መክሊት ብርና ሠላሳ መክሊት ወርቅ ጫነበት።


የከንፈር ቃል ለሰልፍ ምክርና ኀይል እንደሚሆን ትናገራለህ፤ አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው?


አሳንም ሊያገኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው “አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ! ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተውት ግን ይተዋችኋል።


ስለ እግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት በጀመረው ሥራ ሁሉ፥ በሕጉና በትእዛዙም፥ አምላኩን ለመፈለግ በፍጹም ልቡ አደረገው፥ ተከናወነለትም።


ይህም ሕዝቅያስ የላይኛውን የግዮንን ውኃ ምንጭ ደፈነ፤ በዳዊትም ከተማ በምዕራብ በኩል አቅንቶ አወረደው። የሕዝቅያስም ሥራ ሁሉ ተከናወነ።


የዘመንህም ጸጥታ የመድኃኒት ብዛት፥ ጥበብና እውቀት ይሆናል፥ እግዚአብሔርን መፍራት መዝገቡ ነው።


እኔ፦ ለሰልፍ የሆነው ምክርህና ኃይልህ ከንቱ ነገር ነው አልሁ፥ አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው?


እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።


እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?


እግዚአብሔርም ከይሁዳ ጋር ነበረ፥ ይሁዳም ተራራማውን አገር ወረሰ፥ በሸለቆው የሚኖሩት ግን የብረት ሰረገሎች ነበሩአቸውና ሊያወጣቸው አልቻለም።


ዳዊትም በአካሄዱ ሁሉ አስተውሎ ያደርግ ነበር፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ።


ዳዊትም ሳኦል ወደ ሰደደው ሁሉ ይሄድ ነበር፥ አስተውሎም ያደርግ ነበር፥ ሳኦልም በጦረኞች ላይ ሾመው፥ ይህም በሕዝብ ሁሉ ዓይንና በሳኦል ባሪያዎች ዓይን መልካም ነበረ።


跟着我们:

广告


广告