Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 18:27 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ራፋስቂስ ግን “ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ አንተና ወደ ጌታህ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ወደ ተቀመጡት ሰዎች አይደለምን?” አላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ነገር ግን የጦር አዛዡ መልሶ፣ “ጌታዬ እነዚህን ቃሎች እንድናገር የላከኝ ለጌታህና ለአንተ ብቻ ነበርን? እንደ እናንተ የራሳቸውን ኵስ ለመብላትና ሽንታቸውንም ለመጠጣት በቅጥሩ ላይ ለተቀመጡት ሰዎችም አይደለምን?” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እርሱም “የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይህን ሁሉ ለእናንተና ለንጉሣችሁ ብቻ እንድናገር የላከኝ መሰላችሁን? ከቶ አይደለም፤ ልክ እንደ እናንተ ኩሳቸውን ለመብላትና ሽንታቸውን ለመጠጣት የሚገደዱ ሰዎችም ጭምር ስለ ሆኑ፥ እኔ የምናገረውን በቅጽሩ ላይ ያሉት ሰዎች ሁሉ እንዲሰሙት ነው” ሲል መለሰላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እርሱም “የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይህን ሁሉ ለእናንተና ለንጉሣችሁ ብቻ እንድናገር የላከኝ መሰላችሁን? ከቶ አይደለም፤ ልክ እንደ እናንተ ኩሳቸውን ለመብላትና ሽንታቸውን ለመጠጣት የሚገደዱ ሰዎችም ጭምር ስለ ሆኑ፥ እኔ የምናገረውን በቅጽሩ ላይ ያሉት ሰዎች ሁሉ እንዲሰሙት ነው” ሲል መለሰላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ራፋ​ስ​ቂስ ግን፥ “በውኑ ጌታዬ ይህን ቃል እና​ገር ዘንድ ወደ እና​ን​ተና ወደ ጌታ​ችሁ ልኮ​ኛ​ልን? ከእ​ና​ንተ ጋር ኵሳ​ቸ​ውን ይበሉ ዘንድ ሽን​ታ​ቸ​ው​ንም ይጠጡ ዘንድ በቅ​ጥር ላይ ወደ ተቀ​መ​ጡት ሰዎች አይ​ደ​ለ​ምን?” አላ​ቸው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 18:27
11 交叉引用  

የአሦርም ንጉሥ ተርታንንና ራፌስን ራፋስቂስንም ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላከ። ወጥተውም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ በመጡም ጊዜ በአጣቢው እርሻ መንገድ ባለችው በላይኛይቱ ኩሬ መስኖ አጠገብ ቆሙ።


የኬልቅያስም ልጅ ኤልያቄም ሳምናስም ዮአስም ራፋስቂስን “እኛ እንሰማለንና እባክህ፥ በሶርያ ቋንቋ ለባሪያዎችህ ተናገር፤ በቅጥርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በአይሁድ ቋንቋ አትናገረን፤” አሉት።


ራፋስቂስም ቆሞ በታላቅ ድምፅ በአይሁድ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ጮኽ “የታላቁን የአሦር ንጉሥ ቃል ስሙ፤ ንጉሡ እንዲህ ይላል


በሰማርያም ታላቅ ራብ ሆኖ ነበር፤ እነሆም፥ የአህያ ራስ በአምሳ ብር፥ የርግብም ኩስ የጎሞር ስምንተኛ የሚሆን በአምስት ብር እስኪሸጥ ድረስ ከበቡአት።


ራፋስቂስ ግን፦ ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ አንተና ወደ ጌታህ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ወደ ተቀመጡ ሰዎች አይደለምን? አላቸው።


ዳሌጥ። ጡት የሚጠባው የሕፃን ምላስ ከጥም የተነሣ ወደ ትናጋው ተጣበቀ፥ ሕፃናት እንጀራ ለመኑ፥ የሚቈርስላቸውም የለም።


ሄ። የጣፈጠ ነገር ይበሉ የነበሩ በመንገድ ጠፉ፥ በቀይ ግምጃ ያድጉ የነበሩ የፍግ ክምር አቀፉ።


እግዚአብሔርም፦ እንዲሁ የእስራኤል ልጆች እነርሱን በምበትንባቸው በአሕዛብ መካከል ርኩስ እንጀራቸውን ይበላሉ አለው።


እርሱም፦ እነሆ፥ በሰው ፋንድያ ፋንታ ኩበት ሰጥቼሃለሁ በእርሱም እንጀራህን ትጋግራለህ አለኝ።


跟着我们:

广告


广告