Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 17:24 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የአሦርም ንጉሥ ከባቢሎንና ከኩታ ከአዋና ከሐማት ከሴፈርዋይም ሰዎችን አመጣ፤ በእስራኤልም ልጆች ፋንታ በሰማርያ ከተሞች አኖራቸው፤ ሰማርያንም ወረሱአት፤ በከተሞችዋም ተቀመጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የአሦርም ንጉሥ ሕዝቡን ከባቢሎን፣ ከኩታ፣ ከአዋና ከሐማት፣ ከሴፈርዋይም ከተሞች አምጥቶ በእስራኤላውያን ቦታ እንዲገቡ በሰማርያ ከተሞች አሰፈራቸው፤ እነርሱም ሰማርያን ወርሰው በከተሞቿ ይኖሩ ጀመር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የአሦር ንጉሠ ነገሥት በባቢሎን፥ ኩታ፥ ዓዋ፥ ሐማትና ሰፋርዋይም ተብለው በሚጠሩት ከተሞች ይኖሩ የነበሩትን አሕዛብ አምጥቶ ተሰደው በሄዱት በእስራኤላውያን እግር በመተካት በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፤ እነርሱም እነዚህን ከተሞች ወርሰው በዚያ መኖር ጀመሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የአሦር ንጉሠ ነገሥት በባቢሎን፥ ኩታ፥ ዓዋ፥ ሐማትና ሰፋርዋይም ተብለው በሚጠሩት ከተሞች ይኖሩ የነበሩትን አሕዛብ አምጥቶ ተሰደው በሄዱት በእስራኤላውያን እግር በመተካት በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፤ እነርሱም እነዚህን ከተሞች ወርሰው በዚያ መኖር ጀመሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኩታ፥ ከአ​ዋና ከሐ​ማት፥ ከሴ​ፌ​ር​ዋ​ይም ሰዎ​ችን አመጣ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፋንታ በሰ​ማ​ርያ ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው፤ ሰማ​ር​ያ​ንም ወረ​ሱ​አት፤ በከ​ተ​ሞ​ች​ዋም ተቀ​መጡ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 17:24
16 交叉引用  

በዚያም ዘመን ሰሎሞን ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ፥ ከሐማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ ያለው ታላቅ ጉባኤ፥ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ሰባት ቀን በዓሉን አደረጉ።


በሆሴዕ በዘጠነኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ወሰደ፤ እስራኤልንም ወደ አሦር አፈለሰ፤ በአላሔና በአቦር በጎዛንም ወንዝ በሜዶንም ከተሞች አኖራቸው።


ሕዝቅያስንም አትስሙ፤’ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል ‘ከእኔ ጋር ታረቁ፤ ወደ እኔም ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፤ ከጕድጓዳችሁም ውሃ ጠጡ፤


የሐማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፈርዋይምና የሄና የዒዋም አማልክት ወዴት አሉ? ሰማርያን ከእጄ አድነዋታልን?


የሐማት ንጉሥ፥ የአርፋድ ንጉሥ፥ የሴፈርዋይም ከተማ ንጉሥ፥ የሄናና የዒዋ ንጉሥ ወዴት አሉ?”


ስለዚህም እግዚአብሔር የአሦርን ንጉሥ ሠራዊት አለቆች አመጣባቸው፤ ምናሴንም በዛንጅር ያዙት፤ በሰንሰለትም አስረው ወደ ባቢሎን ወሰዱት።


ካልኖ እንደ ከርከሚሽ አይደለችምን? ሐማትስ እንደ አርፋድ አይደለችምን? ሰማርያስ እንደ ደማስቆ አይደለችምን?


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከጳትሮስና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላምና ከሰናዖር ከሐማትም፥ ከባሕርም ደሴቶች ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደገና እጁን ይገልጣል።


የሐማትና የአልፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፈርዋይም አማልክት ወዴት አሉ? ሰማርያን ከእጄ አድነዋታልን?


የሐማት ንጉሥ፥ የአርፋድ ንጉሥ፥ የሴፈርዋይም ከተማ ንጉሥ፥ የሄናና የዒዋ ንጉሥ ወዴት አሉ?


አቤቱ፥ በእውነት የአሦር ነገሥታት ዓለሙን ሁሉ አገሮቻቸውንም አፍርሰዋል፥


ይህም የሆነው ንጉሡ ሴዴቅያስ፦ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይወጋናልና ስለ እኛ፥ እባክህ፥ እግዚአብሔርን ጠይቅ፥ ከእኛም ይመለስ ዘንድ ምናልባት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ ተአምራቱ ሁሉ ያደርግ ይሆናል ብሎ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስ ወደ ኤርምያስ በላከ ጊዜ ነው።


እግዚአብሔር ስለ ከለዳውያን ምድር ስለ ባቢሎን በነቢዩ በኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው።


እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፥ እንዲህም አለ፦ በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤


跟着我们:

广告


广告