Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 17:22 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22-23 የእስራኤልም ልጆች ኢዮርብዓም ባደረገው ኀጢአት ሁሉ ሄዱ፤ እግዚአብሔርም በባሪያዎቹ በነቢያቱ ሁሉ አፍ እንደ ተናገረው እስራኤልን ከፊቱ እስኪያወጣ ድረስ ከእርስዋ አልራቁም። እስራኤልም እስከ ዛሬ ድረስ ከምድሩ ወደ አሦር ፈለሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እስራኤላውያንም በኢዮርብዓም ኀጢአት ሁሉ ጸኑ፤ ከዚያም አልተመለሱም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እስራኤላውያንም በኢዮርብዓም ኀጢአት ሁሉ ጸኑ፤ ከዚያም አልተመለሱም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22-23 በአገልጋዮቹ በነቢያት ሁሉ አማካይነት እግዚአብሔር እስራኤልን ከፊቱ እስኪያስወግድ ድረስ እስራኤላውያን የኢዮርብዓምን ኃጢአት ሲሠሩ ኖሩ እንጂ ከዚያ አልራቁም። ስለዚህ እስራኤላውያን ከሀገራቸው ተማርከው በመወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ በአሦር ይኖራሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኢዮ​ር​ብ​ዓም ባደ​ረ​ገው ኀጢ​አት ሁሉ ሄዱ፤

参见章节 复制




2 ነገሥት 17:22
10 交叉引用  

ነገር ግን እስራኤልን ካሳተው ከናባጥ ልጅ ከኢዮርብዓም ኀጢአት፥ በቤቴልና በዳን ከነበሩት ከወርቁ እምቦሶች፥ ኢዩ አልራቀም።


ኢዩ ግን በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ሕግ በፍጹም ልቡ ይሄድ ዘንድ አልተጠነቀቀም፤ እስራኤልንም ካሳተው ከኢዮርብዓም ኀጢአት አልራቀም።


በእግዚአብሔር ፊት ክፋ ነገር አደረገ፤ እስራኤልን በሳተው በናባጥ ልጅ በኢዮርብዓም ኀጢአት ሁሉ ሄደ እንጂ ከእርስዋ አልራቀም።


በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ እስራኤልንም ያሳተውን የናባጥን ልጅ የኢዮርብዓምን ኀጢአት ተከተለ፤ ከእርስዋም አልራቀም።


ነገር ግን በእርስዋ ሄዱ እንጂ እስራኤልን ካሳተው ከኢዮርብዓም ቤት ኀጢአት አልራቁም፤ ደግሞም የማምለኪያ ዐፀድ በሰማርያ ቆሞ ቀረ።


አባቶቹም እንዳደረጉት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ እስራኤልን ካሳታቸው ከናባጥ ልጅ ከኢዮርብዓም ኀጢአት አልራቀም።


እስራኤልንም ከዳዊት ቤት ለየ፤ የናባጥንም ልጅ ኢዮርብዓምን አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እግዚአብሔርን ከመከተል እስራኤልን መለሰ፤ ታላቅም ኀጢአት አሠራቸው።


ነገር ግን እስራኤልን ባሳታቸው በናባጥ ልጅ በኢዮርብዓም ኀጢአት ተያዘ፤ ከእርሱም አልራቀም።


የዳንም ልጆች የተቀረጸውን ምስል ለራሳቸው አቆሙ፥ የሙሴም ልጅ የጌርሳም ልጅ ዮናታን፥ እርሱና ልጆቹ የአገሩ ሰዎች እስከሚማረኩበት ቀን ድረስ የዳን ነገድ ካህናት ነበሩ።


跟着我们:

广告


广告