Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 17:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሥርዐቱንም፥ ከአባቶቻቸውም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን፥ ያጸናላቸውንም ምስክሩን ናቁ፤ ከንቱ ነገርንም ተከተሉ፤ ምናምንቴዎችም ሆኑ፤ እግዚአብሔርም እንደ እነርሱ እንዳይሠሩ ያዘዛቸውን በዙሪያቸው ያሉትን አሕዛብ ተከተሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሥርዐቱንና ከአባቶቻቸው ጋራ የገባውን ኪዳን፣ ለእነርሱም የሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ናቁ፤ ከንቱ ጣዖታትን ተከትለው ራሳቸውም ከንቱ ሆኑ፤ እግዚአብሔር፣ “እነርሱ የሚያደርጉትን እንዳታደርጉ” ብሎ ቢያዝዛቸው እንኳ በዙሪያቸው ያሉትን አሕዛብ ተከተሉ፤ እግዚአብሔር እንዳያደርጉ የከለከላቸውንም ፈጸሙ እንጂ አልተዉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የሰጣቸውንም ድንጋጌ አልተቀበሉም፤ ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ የሰጣቸውንም ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ቸል አሉ፤ ለከንቱ ጣዖቶች በመስገድ ራሳቸውም ከንቱዎች ሆኑ፤ የእነርሱን መጥፎ ምሳሌነት እንዳይወርሱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዝ በመሻር በዙሪያቸው የሚኖሩ የአሕዛብን ልማድ ሁሉ ተከተሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የሰጣቸውንም ድንጋጌ አልተቀበሉም፤ ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ የሰጣቸውንም ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ቸል አሉ፤ ለከንቱ ጣዖቶች በመስገድ ራሳቸውም ከንቱዎች ሆኑ፤ የእነርሱን መጥፎ ምሳሌነት እንዳይወርሱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዝ በመሻር በዙሪያቸው የሚኖሩ የአሕዛብን ልማድ ሁሉ ተከተሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የገ​ባ​ላ​ቸ​ው​ንም ቃል ኪዳን ሁሉ አል​ጠ​በ​ቁም። ከንቱ ነገ​ር​ንም ተከ​ተሉ፤ ከን​ቱም ሆኑ፤ እንደ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሠሩ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያሉ​ትን አሕ​ዛብ ተከ​ተሉ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 17:15
40 交叉引用  

እግዚአብሔርም ሰሎሞንን አለው “ይህን ሠርተሃልና፥ ያዘዝሁህንም ቃል ኪዳኔንና ሥርዐቴን አልጠበቅህምና መንግሥትህን ከአንተ ቀዳድጄ ለባሪያህ እሰጠዋለሁ።


እግዚአብሔርም ከእስራኤል ልጆች ፊት ባሳደዳቸው በአሕዛብ ሥርዐት፥ የእስራኤልም ነገሥታት ባደረጓት ሥርዐት ሄደው ነበርና እንደዚህ ሆነ።


ወደ እግዚአብሔርም ይመልሱአቸው ዘንድ ነቢያትን ይሰድድላቸው ነበር፤ መሰከሩባቸውም፤ እነርሱ ግን አላደመጡም።


እግዚአብሔርም ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳወጣቸው እንደ አሕዛብ ያለ ርኵሰት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ።


ምናሴም እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ ክፉ ይሠሩ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳተ።


ነገር ግን እንቢተኞች ነበሩ፥ ዐመፁብህም፥ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፥ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፥ እጅግም አስቈጡህ።


እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ትእዛዞቼንና ሕጎቼን ለመጠበቅ እስከ መቼ እንቢ ትላላችሁ?


እነርሱ ምናምንቴና የቀልድ ሥራ ናቸው፥ በተጐበኙ ጊዜ ይጠፋሉ።


በአንድ ጊዜ ሰንፈዋል፥ ደንቍረውማል፥ ጣዖታት የሚያስተምሩት የእንጨት ነገር ብቻ ነው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁ ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ ከንቱነትንም የተከተሉ፥ ከንቱም የሆኑ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው?


ከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፥ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር።


እግዚአብሔርም ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኵሰት ይታገሥ ዘንድ አልቻለም፥ ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ መደነቂያም መረገሚያም ሆናለች ዛሬም እንደ ሆነ የሚኖርባት የለም።


ስላጠናችሁ፥ በእግዚአብሔርም ላይ ስለ በደላችሁ፥ የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልሰማችሁ፥ በሕጉና በሥርዓቱም በምስክሩም ስላልሄዳችሁ፥ ስለዚህ ዛሬ እንደ ሆነ ይህች ክፉ ነገር አግኝታችኋለች።


በማለዳም ተነሥቼ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ሰደድሁባችሁና፦ እንደዚህ እንደ ጠላሁት ያለ ርኩስ ነገር አታድርጉ አልኋችሁ።


ሰውነታችሁንም ታጠፉ ዘንድ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ ትሆኑ ዘንድ፥ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብጽ ምድር ለሌሎች አማልክት በማጠናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?


ነገር ግን አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፥ አባቶቻቸውም ካደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።


ጥበበኞች አፍረዋል ደንግጠውማል ተማርከውማል፥ እነሆ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል፥ ምን ዓይነት ጥበብ አላቸው?


የሰው ልጅ ሆይ፥ በዓመፀኛ ቤት መካከል ተቀምጠሃል፥ ያዩ ዘንድ ዓይን አላቸው እነርሱም አያዩም፥ ይሰሙም ዘንድ ጆሮ አላቸው እነርሱም አይሰሙም፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእኔ ላይ ወደ ዐመፁ ወደ ዓመፀኞች ሰዎች ወደ እስራኤል ልጆች እልክሃለሁ። እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐመፁብኝ።


ሥርዓቴንም ብትንቁ፥ ትእዛዛቴንም ሁሉ እንዳታደርጉ፥ ቃል ኪዳኔንም እንድታፈርሱ ነፍሳችሁ ፍርዴን ብትጸየፍ፥


አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም።


እንግዲህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት፥ ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደ ሆነ ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።


ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፥ ምዋርተኛም፥ ሞራ ገላጭም፥


አሕዛብ ሁሉ፦ እግዚአብሔር በዚህች ምድር ስለ ምን እንደዚህ አደረገ? ይህስ የቁጣው ታላቅ መቅሠፍት ምንድር ነው? ይላሉ።


አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ ቍ 15 በዕብራይስጥ ይሹሩን የሚለውን ግዕዙ ያዕቆብ ይለዋል። 2 በምናምንቴዎቻቸውም አስቈጡኝ፤ 2 እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ 2 በማያስተውል ሕዝብ አስቈጣቸዋለሁ።


አምላካችን እንደ አማልክቶቻቸው አይደለም፤ 2 ጠላቶቻችንም ሰነፎች ናቸው።


ምናምንቴ ነውና የማይረባንና የማያድን ከንቱን ነገር ለመከተል ፈቀቅ አትበሉ።


跟着我们:

广告


广告