Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 17:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እግዚአብሔርም የከለከላቸውን ጣዖቶች አመለኩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግዚአብሔር፣ “ይህን ማድረግ አይገባችሁም” ቢላቸውም እንኳ እነርሱ ጣዖታትን አመለኩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እግዚአብሔር ለጣዖት እንዳይሰግዱ ያዘዛቸውንም ሕግ ሁሉ አፈረሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር ለጣዖት እንዳይሰግዱ ያዘዛቸውንም ሕግ ሁሉ አፈረሱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ይህን አታ​ድ​ርጉ” ብሎ የከ​ለ​ከ​ላ​ቸ​ውን ጣዖ​ቶች አመ​ለኩ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 17:12
13 交叉引用  

በሚመጣውም ዓመት ወልደ አዴር ሶርያውያንን አሰለፈ፥ ከእስራኤልም ጋር ይዋጋ ዘንድ ወደ አፌቅ ወጣ።


እግዚአብሔርም ከፊታቸው ያወጣቸው አሕዛብ እንዳደረጉት፥ በኮረብቶቹ መስገጃዎች ሁሉ ላይ ያጥኑ ነበር፤ እግዚአብሔርንም ያስቆጡ ዘንድ ክፉ ነገር አደረጉ፤


ነገር ግን እንደ ቀደመው ልማዳቸው አደረጉ እንጂ አልሰሙም።


ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ።


ስሙ ቀናተኛ የሆነ እግዚአብሔር ቅንዓት ያለው አምላክ ነውና ለሌላ አምላክ አትስገድ።


እሰጣቸውም ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ባገባኋቸው ጊዜ፥ ከፍ ያለውን ኮረብታ ሁሉ ቅጠልማውንም ዛፍ ሁሉ አዩ፥ በዚያም መሥዋዕታቸውን ሠዉ በዚያም የሚያስቈጣኝን ቍርባናቸውን አቀረቡ በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ በዚያም የመጠጥ ቍርባናቸውን አፈሰሱ።


እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።


ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር እንዲህ ያለ ሥራ አትሥሩ።


በእናንተ መካከል ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ አትግቡ፥ የአማልክቶቻቸውንም ስም አትጥሩ፥ አትማሉባቸውም፥ አታምልኩአቸውም፥ አትስገዱላቸውም፥


跟着我们:

广告


广告