Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 15:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የሠራዊቱም አለቃ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ተማማለበት፤ በሰማርያም በንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ከአርጎብና ከአርያ ጋር መታው፤ ከእርሱም ጋር አምሳ የገለዓድ ሰዎች ነበሩ፤ ገደለውም፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከጦር አለቆቹ አንዱ የሆነው የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ አሤረበት፤ ዐምሳ የገለዓድ ሰዎች ይዞ በመሄድ፣ ሰማርያ ቤተ መንግሥት ባለው ምሽግ ፋቂስያስን ከአርጎብና ከአርያ ጋራ ገደለው፤ በእግሩም ተተክቶ ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ከፈቃሕያ ሠራዊት መካከል ፈቁሔ ተብሎ የሚጠራ የረማልያ ልጅ የሆነ አንድ የጦር መኰንን ከኀምሳ የገለዓድ ሰዎች ጋር ሆኖ ሤራ ጠነሰሰ፤ በሰማርያ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በሚገኘው ምሽግ ውስጥ ዘልቆ በመግባትም ፈቃሕያን ከአርጎብና ከሃርዬ ጋር ገድሎ በፈቃሕያ እግር ተተክቶ ነገሠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ከፈቃሕያ ሠራዊት መካከል ፈቁሔ ተብሎ የሚጠራ የረማልያ ልጅ የሆነ አንድ የጦር መኰንን ከኀምሳ የገለዓድ ሰዎች ጋር ሆኖ ሤራ ጠነሰሰ፤ በሰማርያ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በሚገኘው ምሽግ ውስጥ ዘልቆ በመግባትም ፈቃሕያን ከአርጎብና ከሃርዬ ጋር ገድሎ በፈቃሕያ እግር ተተክቶ ነገሠ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ከዳው፤ በሰ​ማ​ር​ያም በን​ጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ከአ​ር​ጎ​ብና ከአ​ርያ ጋር መታው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ከገ​ለ​ዓ​ዳ​ው​ያን አምሳ ሰዎች ነበሩ፤ ገደ​ለ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ነገሠ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 15:25
10 交叉引用  

ዘምሪም ከተማይቱ እንደ ተያዘች ባየ ጊዜ ወደ ንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ገባ፤ የንጉሡንም ቤት በራሱ ላይ በእሳት አቃጠለ፤


የእኩሌቶቹም ሠረገሎች አለቃ ዘምሪ ተማማለበት፤ ኤላም በቴርሳ ነበረ፤ በቴርሳም በነበረው በቤት አሽከሮች አለቃ በአሳ ቤት ይሰክር ነበር።


የኢያቤስም ልጅ ሰሎም ተማማለበት፤ በይብልዓም መትቶ ገደለው፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።


በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ እስራኤልን ካሳተው ከናባጥ ልጅ ከኢዮርብዓም ኀጢአት አልራቀም።


የቀረውም የፋቂስያስ ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።


በይሁዳ ንጉሥ በዓዛርያስ በአምሳ ሁለተኛው ዓመት የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በእስራኤል ላይ በሰማርያ መንገሥ ጀመረ፤ ሃያ ዓመትም ነገሠ።


እንዲሁም የናሜሲ ልጅ የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዩ በኢዮራም ላይ ተማማለ። ኢዮራምና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል የተነሣ ሬማት ዘገለዓድን ይጠብቁ ነበር።


በገባም ጊዜ፥ እነሆ፥ የሠራዊት አለቆች ተቀምጠው ነበር፤ እርሱም “አለቃ ሆይ! ለአንተ መልእክት አለኝ፤” አለ። ኢዩም “ለማንኛችን ነው?” አለ። እርሱም “አለቃ ሆይ! ለአንተ ነው፤” አለ።


የአባቶቻቸውንም አምላክ እግዚአብሔርን ትተው ነበርና የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በአንድ ቀን ከይሁዳ መቶ ሃያ ሺህ ገደለ፤ ሁሉም ጽኑአን ነበሩ።


እንዲህም ሆነ፥ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ልጅ በኢዮአታም ልጅ በአካዝ ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የእስራኤልም ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፥ ሊያሸንፉአትም አልቻሉም።


跟着我们:

广告


广告