Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 13:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ነገር ግን በእርስዋ ሄዱ እንጂ እስራኤልን ካሳተው ከኢዮርብዓም ቤት ኀጢአት አልራቁም፤ ደግሞም የማምለኪያ ዐፀድ በሰማርያ ቆሞ ቀረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ይሁን እንጂ እስራኤልን ከአሳተው ከኢዮርብዓም ቤት ኀጢአት አልተመለሱም፤ በዚያው ገፉበት እንጂ። የአሼራም ምስል ዐምድ በሰማርያ መመለኩ ቀጠለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ኢዮርብዓም እስራኤልን ወደ ኃጢአት ከመራበት ከበደል ሥራቸው አልተመለሱም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ በኃጢአታቸው ጸንተው አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስል በሰማርያ ማምለክ ቀጠሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ኢዮርብዓም እስራኤልን ወደ ኃጢአት ከመራበት ከበደል ሥራቸው አልተመለሱም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ በኃጢአታቸው ጸንተው አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስል በሰማርያ ማምለክ ቀጠሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ነገር ግን በእ​ር​ስዋ ሄዱ እንጂ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተ​በት ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ኀጢ​አት አል​ራ​ቁም፤ ደግ​ሞም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ በሰ​ማ​ርያ ቆሞ ነበረ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 13:6
15 交叉引用  

ስለ በደለውና እስራኤልንም ስላሳተበት ስለ ኢዮርብዓም ኀጢአት እስራኤልን ይጥላል።”


ከእርሱ አስቀድሞ ባደረገው በአባቱ ኀጢአት ሁሉ ሄደ፤ ልቡም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም አልነበረም።


በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም መንገድ ሁሉ በምናምንቴም ነገራቸው የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ያስቆጡት ዘንድ እስራኤልን ባሳተበት ኀጢአት ሄደ።


አክዓብም የማምለኪያ ዐፀድ ተከለ፤ አክዓብም ከእርሱ በፊት ከነበሩት ሁሉ ይልቅ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚያስቆጣውን ነገር አበዛ።


ነገር ግን እስራኤልን ካሳተው ከናባጥ ልጅ ከኢዮርብዓም ኀጢአት፥ በቤቴልና በዳን ከነበሩት ከወርቁ እምቦሶች፥ ኢዩ አልራቀም።


በእግዚአብሔር ፊት ክፋ ነገር አደረገ፤ እስራኤልን በሳተው በናባጥ ልጅ በኢዮርብዓም ኀጢአት ሁሉ ሄደ እንጂ ከእርስዋ አልራቀም።


በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ እስራኤልንም ያሳተውን የናባጥን ልጅ የኢዮርብዓምን ኀጢአት ተከተለ፤ ከእርስዋም አልራቀም።


የአምላካቸውንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ተዉ፤ ቀልጠው የተሠሩትንም የሁለቱን እንቦሶች ምስሎች አደረጉ፤ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከሉ፤ ለሰማይ ሠራዊትም ሁሉ ሰገዱ፤ በኣልንም አመለኩ።


በኮረብታም ያሉትን መስገጃዎች አስወገደ፤ ሐውልቶችንም ቀለጣጠመ፤ ያማምለኪያ ዐፀዶችንም ቈረጠ፤ የእስራኤልም ልጆች እስከዚህ ዘመን ድረስ ያጥኑለት ነበርና ሙሴ የሠራውን የናሱን እባብ ሰባበረ፤ ስሙንም “ነሑሽታን” ብሎ ጠራው።


አባቱ ሕዝቅያስም ያፈረሳቸውን የኮረብታውን መስገጃዎች መልሶ ሠራ፤ የእስራኤልም ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ለበኣል መሠዊያ ሠራ፤ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከለ፤ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገደ፤ አመለካቸውም።


ንጉሡም የካህናቱን አለቃ ኬልቅያስን በሁለተኛውም መዓርግ ያሉትን ካህናትን በረኞቹንም ለባአልና ለማምለኪያ ዐፀድ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የተሠሩትን ዕቃዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር መቅደስ ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው፤ ከኢየሩሳሌምም ውጭ በቄድሮን ሜዳ አቃጠላቸው፤ አመዱንም ወደ ቤቴል ወሰደው።


ለኃጢአተኛ ሞገስ ቢደረግለት ጽድቅን አይማርም፥ በቅኖች ምድር ክፉን ነገር ያደርጋል፥ የእግዚአብሔርንም ግርማ አያይም።


ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፤ መሠዊያቸውን አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም በእሳት አቃጥሉ።


跟着我们:

广告


广告