Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 12:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የቀረውም የኢዮአስ ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሹማምቱም በርሱ ላይ ዐመፁበት፤ ቍልቍል ወደ ሲላ በሚወስደው መንገድ ላይ በቤት ሚሎ ገደሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የቀረውም የኢዮአስ ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20-21 ከዚህ በኋላ የንጉሥ ኢዮአስ ባለሟሎች የሆኑ ባለሥልጣኖች አደሙበት፤ ከእነርሱም ሁለቱ የሺምዓት ልጅ ዮዛካርና የሾሜር ልጅ ይሆዛባድ ወደ ሲላ በሚወስደው ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በተደለደለ መሬት ላይ በተሠራው ቤት ገደሉት፤ ኢዮአስም በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አሜስያስ ነገሠ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ተነ​ሥ​ተው ዐመ​ፁ​በት፥ ወደ ሲላ በሚ​ወ​ር​ደ​ውም መን​ገድ በመ​ሀሎ ቤት ኢዮ​አ​ስን ገደ​ሉት።

参见章节 复制




2 ነገሥት 12:20
11 交叉引用  

ዳዊትም በአምባይቱ ውስጥ ተቀመጠ፥ የዳዊትም ከተማ ብሎ ጠራት። ዳዊትም ዙሪያዋን ከሚሎ ጀምሮ ወደ ውስጥ ቀጠራት።


በንጉሡም ያመፀበት ምክንያት ይህ ነው፤ ሰሎሞን ሚሎን ሠራ፤ የአባቱንም የዳዊትን ከተማ ሰባራውን ጠገነ።


የቀረውም የሮብዓም ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?


የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአስ አባቶቹ የይሁዳ ነገሥታት ኢዮሣፍጥና ኢዮራም አካዝያስም የቀደሱትን ቅዱስ ነገር፥ እርሱም የቀደሰውን፥ በእግዚአብሔርም ቤትና በንጉሡ ቤተ መዛግብት የተገኘውን ወርቅ ሁሉ ወሰደ፤ ወደ ሶርያም ንጉሥ ወደ አዛሄል ላከው። እርሱም ከኢየሩሳሌም ተመለሰ።


መንግሥቱም በጸናለት ጊዜ አባቱን የገደሉትን ባሪያዎች ገደለ።


የአሞንም ባሪያዎች አሴሩበት፤ ንጉሡንም በቤቱ ውስጥ ገደሉት፤


የተረፈውም የኢዮራም ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?


አሜስያስም እግዚአብሔርን ከመከተል ከራቀ በኋላ በኢየሩሳሌም የዓመፅ መሐላ አደረጉበት፤ ወደ ለኪሶም ኵበለለ፤ በስተ ኋላውም ወደ ለኪሶ ላኩ፤ በዚያም ገደሉት።


ባሪያዎቹም ተማምለው በቤቱ ገደሉት።


የሴኬምም ሰዎች ሁሉ ቤትሚሎም ሁሉ ተሰበሰቡ፥ ሄደውም በሴኬም በዓምዱ አጠገብ ባለው በአድባሩ ዛፍ በታች አቤሜሌክን አነገሡ።


跟着我们:

广告


广告