Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 12:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በሣጥንም ውስጥ ብዙ ገንዘብ መኖሩን ባዩ ጊዜ የንጉሡ ጸሐፊና የካህናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን ቈጥረው በከረጢት ውስጥ ያኖሩት ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የገንዘቡ ልክም ተመዝኖ ከታወቀ በኋላ፣ የቤተ መቅደሱን ሥራ በኀላፊነት እንዲያሠሩ ለተመደቡት ሰዎች ገንዘቡን ያስረክቧቸዋል፤ ይህም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለሚሠሩ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችና ግንበኞች፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ትክክለኛውንም ሒሳብ አጣርተው ከመዘገቡ በኋላ ለቤተ መቅደሱ እድሳት ሥራ ኃላፊዎች ያስረክቡ ነበር፤ እነርሱም ገንዘቡን ተረክበው ለአናጢዎችና፥ ለግንበኞች ይሰጡ ነበር፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ትክክለኛውንም ሒሳብ አጣርተው ከመዘገቡ በኋላ ለቤተ መቅደሱ እድሳት ሥራ ኀላፊዎች ያስረክቡ ነበር፤ እነርሱም ገንዘቡን ተረክበው ለአናጢዎችና፥ ለግንበኞች ይሰጡ ነበር፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የተ​ሰ​በ​ሰ​በ​ው​ንም ገን​ዘብ ሥራ​ውን በሚ​ሠ​ሩና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት በሚ​ጠ​ብ​ቁት እጅ ይሰጡ ነበር። እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለሚ​ሠሩ ግን​በ​ኞ​ችና አና​ጢ​ዎች ይሰጡ ነበር።

参见章节 复制




2 ነገሥት 12:11
6 交叉引用  

የጢሮስም ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መልእክተኞችን የዝግባ እንጨትንም አናጢዎችንም ጠራቢዎችንም ላከ፥ ለዳዊትም ቤት ሠሩለት።


ካህኑ ዮዳሄ ግን ሣጥን ወስዶ መክደኛውን ነደለው፤ በመሠዊያውም አጠገብ ወደ እግዚአብሔር ቤት በሚገቡበት መግቢያ በስተ ቀኝ አኖረው፤ ደጁንም የሚጠብቁ ካህናት ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመጣውን ገንዘብ ሁሉ ያኖሩበት ነበር።


የተመዘነውንም ገንዘብ የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት በተሾሙት እጅ ይሰጡ ነበር።


跟着我们:

广告


广告