Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 10:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 መልእክተኛም መጥቶ “የንጉሡን ልጆች ራሶች ይዘው መጥተዋል፤” ብሎ ነገረው። እርሱም “እስከ ነገ ድረስ በበሩ አደባባይ ሁለት ክምር አድርጋችሁ አኑሩአቸው፤” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 መልእክተኛው እንደ ደረሰም፣ ለኢዩ፣ “የንጉሡን ልጆች ራስ አምጥተዋል” ብሎ ነገረው። ከዚያም ኢዩ፣ “በከተማዪቱ መግቢያ በር ላይ ሁለት ቦታ ከምራችሁ እስከ ነገ ጧት ድረስ አቈዩአቸው” ብሎ አዘዘ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ኢዩ የአክዓብ ትውልድ ራሶች ተቆርጠው መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በከተማይቱ ቅጽር በር በሁለት ረድፍ ተከምረው እስከ ተከታዩ ቀን ጧት ድረስ እንዲቆዩ ትእዛዝ ሰጠ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ኢዩ የአክዓብ ትውልድ ራሶች ተቈርጠው መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በከተማይቱ ቅጽር በር በሁለት ረድፍ ተከምረው እስከ ተከታዩ ቀን ጧት ድረስ እንዲቈዩ ትእዛዝ ሰጠ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 መል​እ​ክ​ተ​ኛም መጥቶ፥ “የን​ጉ​ሡን ልጆች ራስ ይዘው መጥ​ተ​ዋል” ብሎ ነገ​ረው። ንጉ​ሡም፥ “እስከ ነገ ድረስ በበሩ አደ​ባ​ባይ ሁለት ክምር አድ​ር​ጋ​ችሁ አኑ​ሩ​አ​ቸው” አለ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 10:8
6 交叉引用  

አክዓብም፦ በማን? አለ፤ እርሱም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአውራጆቹ አለቆች ጕልማሶች አለ፤ እርሱም፦ ሰልፉን ማን ይጀምራል? አለ፤ እርሱም፦ አንተ አለው።


ደብዳቤውም በደረሳቸው ጊዜ የንጉሡን ልጆች ሰባውን ሰዎች ይዘው ገደሉአቸው፤ ራሶቻቸውንም በቅርጫት አድርገው ወደ እርሱ ወደ ኢይዝራኤል ላኩ።


በነጋውም ወጥቶ ቆመ፤ ሕዝቡንም ሁሉ “እናንተ ንጹሐን ናችሁ፤ እነሆ፥ ጌታዬን የወነጀልሁ የገደልሁትም እኔ ነኝ፤ እነዚህንስ ሁሉ የገደለ ማን ነው?


ራሱንም በወጭት አምጥቶ ለብላቴናይቱ ሰጣት፥ ብላቴናይቱም ለእናትዋ ሰጠች።


በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና ሬሳው በእንጨት ላይ አይደር፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር እንዳታረክስ በእርግጥ በዚያው ቀን ቅበረው።


跟着我们:

广告


广告