Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 10:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሁለተኛም “ወገኖቼስ እንደ ሆናችሁ፥ ነገሬንም ከሰማችሁ፥ የጌታችሁን ልጆች ራሶች ቍረጡ፤ ነገም በዚህ ሰዓት ወደ ኢይዝራኤል ወደ እኔ ይዛችሁ ኑ፤” ብሎ ደብዳቤ ጻፈላቸው። የንጉሡም ልጆች ሰባው ሰዎች በሚያሳድጓቸው በከተማይቱ ታላላቆች ዘንድ ነበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከዚያም ኢዩ፣ “እንግዲህ የእኔ ወገን ከሆናችሁና ከታዘዛችሁኝ የጌታችሁን ልጆች ራስ ቈርጣችሁ ነገ በዚህ ሰዓት ይዛችሁልኝ ወደ ኢይዝራኤል እንድትመጡ” ሲል ደግሞ ጻፈላቸው። በዚህም ጊዜ ሰባው የንጉሡ ልጆች በከተማዪቱ ውስጥ ታዋቂ በሆኑ አሳዳጊዎቻቸው ዘንድ ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ኢዩም “እናንተ ከእኔ ጋር ከተባበራችሁና ትእዛዜንም ለመፈጸም ዝግጁዎች ከሆናችሁ፥ ነገ በዚህ ጊዜ የንጉሥ አክዓብን ዘሮች ሁሉ ራሶቻቸውን ቆርጣችሁ ይዛችሁልኝ ኑ” ሲል ሌላ ደብዳቤ ጻፈላቸው። ሰባው የንጉሥ አክዓብ ተወላጆች በሰማርያ አሳዳጊዎቻቸው በሆኑ በታወቁ የአገር ሽማግሌዎች ጥበቃ ሥር ነበሩ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ኢዩም “እናንተ ከእኔ ጋር ከተባበራችሁና ትእዛዜንም ለመፈጸም ዝግጁዎች ከሆናችሁ፥ ነገ በዚህ ጊዜ የንጉሥ አክዓብን ዘሮች ሁሉ ራሶቻቸውን ቈርጣችሁ ይዛችሁልኝ ኑ” ሲል ሌላ ደብዳቤ ጻፈላቸው። ሰባው የንጉሥ አክዓብ ተወላጆች በሰማርያ አሳዳጊዎቻቸው በሆኑ በታወቁ የአገር ሽማግሌዎች ጥበቃ ሥር ነበሩ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ከዚ​ህም በኋላ ኢዩ፥ “ወገ​ኖ​ቼስ ከሆ​ና​ችሁ፥ ነገ​ሬ​ንም ከሰ​ማ​ችሁ የጌ​ታ​ች​ሁን ልጆች ራስ ቍረጡ፤ ነገም በዚህ ሰዓት ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወደ እኔ ይዛ​ችሁ ኑ” ብሎ ሁለ​ተኛ ደብ​ዳቤ ጻፈ​ላ​ቸው። የን​ጉ​ሡም ልጆች ሰባው ሰዎች በሚ​ያ​ሳ​ድ​ጓ​ቸው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ታላ​ላ​ቆች ዘንድ ነበሩ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 10:6
13 交叉引用  

የቤቱ አለቃ፥ የከተማይቱም አለቃ፥ ሽማግሌዎችና ልጆቹን የሚያሳድጉ “እኛ ባሪያዎችህ ነን፤ ያዘዝኸንንም ሁሉ እናደርጋለን፤ ንጉሥም በላያችን አናነግሥም፤ የምትወድደውን አድርግ፤” ብለው ወደ ኢዩ ላኩ።


ደብዳቤውም በደረሳቸው ጊዜ የንጉሡን ልጆች ሰባውን ሰዎች ይዘው ገደሉአቸው፤ ራሶቻቸውንም በቅርጫት አድርገው ወደ እርሱ ወደ ኢይዝራኤል ላኩ።


በነጋውም ወጥቶ ቆመ፤ ሕዝቡንም ሁሉ “እናንተ ንጹሐን ናችሁ፤ እነሆ፥ ጌታዬን የወነጀልሁ የገደልሁትም እኔ ነኝ፤ እነዚህንስ ሁሉ የገደለ ማን ነው?


ፊቱንም ወደ መስኮቱ አንሥቶ “ከእኔ ጋር ማን ነው?” አለ። ሁለት ሦስትም ጃንደረቦች ወደ እርሱ ተመለከቱ።


እናንተ፦ እግዚአብሔር በደላቸውን ለልጆቻቸው ይጠብቃል ብላችኋል። እነርሱ ያውቁ ዘንድ ፍዳን ለራሳቸው ይክፈል።


እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የእግዚአብሔር የቍጣው ጽናት ከእስራኤል እንዲመለስ የሕዝቡን አለቆች ሁሉ ወስደህ በፀሐዩ ፊት ወደ እግዚአብሔር ስቀላቸው አለው።


ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፥ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል።


ኢየሱስ ግን፦ የማይቃወማችሁ ከእናንተ ጋር ነውና አትከልክሉት አለው።


በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤ ለሚወድዱኝ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኛና አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም።


跟着我们:

广告


广告