Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 10:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ኢዩም ወደ እስራኤል ሁሉ ላከ፤ የበኣልም አገልጋዮች ሁሉ መጡ፤ ሳይመጣ የቀረ አንድ ስንኳ አልነበረም። ወደ በኣልም ቤት ገቡ፤ የበኣልም ቤት ከዳር እስከ ዳር ድረስ ሞልቶ ነበር፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከዚያም ኢዩ በመላው እስራኤል መልእክት ላከ፤ የበኣል አገልጋዮች በሙሉ መጡ፤ ማንም አልቀረም፤ ሁሉም ወደ በኣል ቤተ ጣዖት ገቡ፤ የበኣል ቤተ ጣዖት ዳር እስከ ዳር ሞላ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ኢዩም በእስራኤል ምድር ሁሉ መልእክት አስተላለፈ፤ በዓልን የሚያመልኩ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ አንድም እንኳ የቀረ ሰው አልነበረም፤ ሁሉም ወደ በዓል ቤተ መቅደስ ገብተው ዳር እስከ ዳር ሞሉት፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ኢዩም በእስራኤል ምድር ሁሉ መልእክት አስተላለፈ፤ ባዓልን የሚያመልኩ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ አንድም እንኳ የቀረ ሰው አልነበረም፤ ሁሉም ወደ ባዓል ቤተ መቅደስ ገብተው ዳር እስከ ዳር ሞሉት፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ኢዩም ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገ​ሮች ሁሉ ላከ፤ የበ​ዓ​ልም አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ፥ ካህ​ና​ቱም ሁሉ፥ ነቢ​ያ​ቶ​ቹም ሁሉ መጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ሳይ​መጣ የቀረ አንድ ሰው እንኳ አል​ነ​በ​ረም። ሁሉም ወደ በዓል ቤት ገቡ፤ የበ​ዓ​ል​ንም ቤት ከዳር እስከ ዳር ድረስ ሞሉት።

参见章节 复制




2 ነገሥት 10:21
7 交叉引用  

በሰማርያም በሠራው በበኣል ቤት ውስጥ ለበኣል መሠዊያ አቆመ።


ዕቃ ቤቱንም “ለበኣል አገልጋዮች ሁሉ ልብስ አውጣ፤” አለው። ልብሱንም አወጣላቸው።


የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በኣል ቤት ሄደው አፈረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን አደቀቁ፤ የበኣልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። ካህኑም ለእግዚአብሔር ቤት አስተዳዳሪዎችን ሾመ።


አሕዛብን ሁሉ ሰብስቤ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፥ በዚያም ስለ ሕዝቤና ስለ ርስቴ ስለ እስራኤል በአሕዛብ መካከል የበተኑአቸውን ምድሬንም የተካፈሉአትን እፋረድባቸዋለሁ።


በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው።


በቤትም ውስጥ ወንዶችና ሴቶች ሞልተውበት ነበር፥ የፍልስጥኤምም መኳንንት ሁሉ በዚያ ነበሩ፥ በቤቱም ሰገነት ላይ ሶምሶን ሲጫወት የሚያዩ ሦስት ሺህ የሚያህሉ ወንዶችና ሴቶች ነበሩ።


跟着我们:

广告


广告