Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 10:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከዚያም በሄደ ጊዜ የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን ተገናኘው፤ ደኅንነቱንም ጠይቆ “ልቤ ከልብህ ጋር እንደ ሆነ ያህል ልብህ ከልቤ ጋር በቅንነት ነውን?” አለው፤ ኢዮናዳብም “እንዲሁ ነው፤” አለው። ኢዩም “እንዲሁ እንደ ሆነስ እጅህን ስጠኝ፤” አለ። እጁንም ሰጠው፤ ወደ ሠረገላውም አውጥቶ ከእርሱ ጋር አስቀመጠውና

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከዚያም ተነሥቶ ሲሄድ የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ወደ እርሱ ሲመጣ መንገድ ላይ አገኘው። ኢዩም ሰላምታ ሰጥቶት “ልቤ ለልብህ ታማኝ የሆነውን ያህል የአንተስ ልብ ለልቤ እንዲሁ ታማኝ ነውን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም፣ “አዎን፤ ነው!” ብሎ መለሰ። ኢዩም፣ “እንግዲያውስ እጅህን ስጠኝ” አለው። እጁንም ሰጠው፤ ከዚያም ኢዩ ደግፎ ወደ ሠረገላው አወጣው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጉዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ “እኔና አንተ በሐሳብ አንድ ነን፤ ታዲያ ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም “አዎ እተባበርሃለሁ” ሲል መለሰ። ኢዩም “እንግዲያውስ ጨብጠኝ” ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠውና፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጒዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ “እኔና አንተ በሐሳብ አንድ ነን፤ ታዲያ ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም “አዎ እተባበርሃለሁ” ሲል መለሰ። ኢዩም “እንግዲያውስ ጨብጠኝ” ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠውና፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከዚ​ያም በሄደ ጊዜ የሬ​ካ​ብን ልጅ ኢዮ​ና​ዳ​ብን በመ​ን​ገድ አገ​ኘው፤ ተቀ​ብ​ሎም መረ​ቀው፤ ኢዩም፥ “ልቤ ከል​ብህ ጋር ቅን እንደ ሆነ ያህል ልብህ ከልቤ ጋር በቅ​ን​ነት ነውን?” አለው። ኢዮ​ና​ዳ​ብም፥ “አዎን” አለው። ኢዩም፥ “እው​ነ​ት​ህስ ከሆነ እጅ​ህን ስጠኝ” አለ። እጁ​ንም ሰጠው፤ ወደ እር​ሱም ወደ ሰረ​ገ​ላው አወ​ጣው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 10:15
20 交叉引用  

ላባም ማልዶ ተነሥቶ ወንዶቹንና ሴቶቹን ልጆቹን ሳመ ባረካቸውም ላባም ተመልሶ ወደ ስፍራው ሄደ።


ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው ከፈርዖንም ፊት ወጣ።


ዮሴፍም ያዕቆብን አባቱን አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቆመው ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው።


ኢዩ ከይሁዳ ንጉሥ ከአካዝያስ ወንድሞች ጋር ተገናኝቶ “እናንተ እነማን ናችሁ?” አለ። እነርሱም “እኛ የአካዝያስ ወንድሞች ነን፤ የንጉሡንና የእቴጌይቱን ልጆች ደኅንነት ለመጠየቅ እንወርዳለን፤” አሉት።


እርሱም “በሕይወታቸው ያዙአቸው!” አለ። ያዙአቸውም፤ በበግ ጠባቂዎችም ቤት አጠገብ ባለው ጕድጓድ አርባ ሁለቱን ሰዎች ገደሉአቸው፤ ማንንም አላስቀረም።


ኢዮራምም “ሠረገላ አዘጋጁ፤” አለ፤ ሠረገላውንም አዘጋጁለት። የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮራም የይሁዳም ንጉሥ አካዝያስ በሠረገሎቻቸው ተቀምጠው ወጡ፤ ኢዩንም ሊገናኙት ሄዱ፤ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ እርሻ ውስጥ አገኙት።


በያቤጽም የተቀመጡ የጸሐፊዎች ወገኖች፤ ቲርዓውያን፥ ሺምዓታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው።


ሚስቶቻቸውን ይፈቱ ዘንድ እጃቸውን ሰጡ፤ ስለ በደላቸውም ከመንጋው አንድ አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት አቀረቡ።


የቤትሐካሪምም ግዛት አለቃ የሬካብ ልጅ መልክያ የጉድፍ መጣያውን በር አደሰ፥ ሠራው፥ ሳንቃዎቹንም አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ።


ወደ ሬካባውያን ቤት ሄደህ ተናገራቸው፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ከጓዳዎቹ ወደ አንዲቱ አግባቸው የወይን ጠጅም አጠጣቸው።


ቃል ኪዳኑንም በማፍረስ መሐላውን ንቆአል፥ እነሆም፥ እጅን ሰጠ፥ ይህንም ሁሉ አድርጎአል፥ ስለዚህ አያመልጥም።


እርሱም፦ “የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል?” አለው። ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው።


ደግሞ የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው፥ አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ኬፋ ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ እነርሱም ወደ ተገረዙት ይሄዱ ዘንድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤


ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ደግሞ እንደ እናንተ ሆኜአለሁና፦ እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ። አንዳችም አልበደላችሁኝም።


跟着我们:

广告


广告