Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ንጉሡም የአምሳ አለቃውን ከአምሳ ሰዎች ጋር ሰደደ፤ ወደ እርሱም ወጣ፤ እነሆም፥ በተራራ ራስ ላይ ተቀምጦ ነበር። እርሱም “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ ‘ውረድ’ ይልሃል፤” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም ንጉሡ አንድ የዐምሳ አለቃ ከዐምሳ ወታደሮቹ ጋራ ወደ ኤልያስ ላከ። የዐምሳ አለቃውም ኤልያስ ወደ ተቀመጠበት ኰረብታ ጫፍ ወጥቶ፣ “አንተ የእግዚአብሔር ሰው፤ ንጉሡ፣ ‘ና ውረድ’ ይልሃል” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከዚህም በኋላ ንጉሡ አንዱን የጦር መኰንን ከኀምሳ ሰዎች ጋር ሄዶ ኤልያስን ይዞ ያመጣለት ዘንድ አዘዘው፤ መኰንኑም ኤልያስን በአንድ ኰረብታ ላይ ተቀምጦ አገኘውና “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ወርደህ ወደ እርሱ እንድትመጣ ንጉሡ አዞሃል” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከዚህም በኋላ ንጉሡ አንዱን የጦር መኰንን ከኀምሳ ሰዎች ጋር ሄዶ ኤልያስን ይዞ ያመጣለት ዘንድ አዘዘው፤ መኰንኑም ኤልያስን በአንድ ኰረብታ ላይ ተቀምጦ አገኘውና “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ወርደህ ወደ እርሱ እንድትመጣ ንጉሡ አዞሃል” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ንጉ​ሡም ይጠ​ሩት ዘንድ የአ​ምሳ አለ​ቃ​ውን ከአ​ምሳ ሰዎች ጋር ወደ እርሱ ላከ፤ ወደ እር​ሱም ሄዱ፤ እነ​ሆም፥ በተ​ራራ ራስ ላይ ተቀ​ምጦ አገ​ኙት። የአ​ምሳ አለ​ቃ​ውም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ ይጠ​ራ​ሃል ፈጥ​ነህ ና፤ ውረድ” አለው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 1:9
22 交叉引用  

እርስዋም ኤልያስን “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለኝ? ኀጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?” አለችው።


አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! ጌታዬ ይፈልግህ ዘንድ ያልላከበት ሕዝብ ወይም መንግሥት የለም፤ ሁሉም ‘በዚህ የለም፤’ ባሉ ጊዜ አንተን እንዳላገኙ መንግሥቱንና ሕዝቡን አምሎአቸው ነበር።


ኤልዛቤልም የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ እርሱ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውሃ ይመግባቸው ነበር።


አክዓብም ሊበላና ሊጠጣ ወጣ፤ ኤልያስም ወደ ቀርሜሎስ አናት ወጣ፤ ፊቱንም በጉልበቱ መካከል አድርጎ በግምባሩ ተደፋ።


ኤልዛቤልም “ነገ በዚህ ጊዜ ነፍስህን ከእነዚህ እንደ አንዲቱ ነፍስ ባላደርጋት፥ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ፤ ይህንም ይጨምሩብኝ፤” ብላ ወደ ኤልያስ መልእክተኛ ላከች።


የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን “እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት የይምላ ልጅ ሚክያስ የሚባል አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ክፉ እንጂ መልካም ትንቢት አይናገርልኝምና እጠላዋለሁ፤” አለው። ኢዮሣፍጥም “ንጉሥ እንዲህ አይበል፤” አለ።


ከዚያም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሰ።


እንዲሁም ሄደች፤ ወደ እግዚአብሔርም ሰው ወደ ቀርሜሎስ ተራራ መጣች። የእግዚአብሔርም ሰው ከሩቅ ባያት ጊዜ ሎሌውን ግያዝን “እነኋት ሱነማዊቲቱ መጣች፤


ወደ እግዚአብሔርም ቤት በበረኛው በሰሎም ልጅ በመዕሤያ ጓዳ በላይ ባለው በአለቆች ጓዳ አጠገብ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ጌዴልያ ልጅ ወደ ሐናን ልጆች ጓዳ አገባኋቸው።


አሜስያስም አሞጽን፦ ባለ ራእዩ ሆይ፥ ሂድ ወደ ይሁዳም ምድር ሽሽ፥ በዚያም እንጀራን ብላ፥


ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና፤


ትንቢት ተናገርልን አሉ።


ከእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፥ በፊቱም ተንበርክከው፦ የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ ዘበቱበት፤


የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና፦ ዋ፥ ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራ፥


አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ አሁን ከመስቀል ይውረድ አሉ። ከእርሱም ጋር የተሰቀሉት ይነቅፉት ነበር።


ደቀ መዛሙርቱም ያዕቆብና ዮሐንስ አይተው፦ ጌታ ሆይ፥ ኤልያስ ደግሞ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዘንድ ትወዳለህን? አሉት።


ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤


ሳኦልም ያንን በሰማ ጊዜ ሌሎች መልእክተኞችን ሰደደ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ። ሳኦልም እንደ ገና ሦስተኛ ጊዜ መልእክተኞችን ሰደደ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ።


跟着我们:

广告


广告