Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 9:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እንግዲህ እንደ በረከት ሆኖ ከስስት የማይሆን ይህ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው፥ አስቀድማችሁ ተስፋ የሰጣችሁትን በረከት አስቀድመው እንዲፈጽሙ ወንድሞችን እለምን ዘንድ እንዲያስፈልገኝ አሰብሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ስለዚህ ወንድሞች አስቀድመው ወደ እናንተ እንዲመጡና ከዚህ በፊት ለመስጠት ቃል የገባችሁትን ስጦታ አጠናቅቃችሁ እንድትጠብቋቸው፣ እነርሱን መለመን አስፈላጊ ሆኖ አግኝቻለሁ፤ እንግዲህ በልግስና ለመስጠት ያሰባችሁት ነገር በግዴታ ሳይሆን በፈቃደኝነት የተዘጋጀ ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እንግዲህ ዝግጁ እንድትሆኑ ወንድሞች አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው፥ አስቀድማችሁ ተስፋ የሰጣችሁትን የልግስና ስጦታ እንደ ግዴታ ሳይሆን በበጎ ፈቃደኝነት ቀደም ብለው እንዲያዘጋጁ፥ እነርሱን መለመን አስፈላጊ መሆኑን አስቤበታለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ስለዚህ ልትሰጡ ቃል የገባችሁበትን የልግሥና ስጦታችሁ በቅድሚያ እንድታዘጋጁ እንዲያስታውሱአችሁ በማለት እነዚህ ወንድሞች ከእኔ ቀድመው ወደ እናንተ እንዲመጡ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ በዚህ ዐይነት እኔ በምመጣበት ጊዜ የልግሥና ስጦታችሁ ዝግጁ ይሆናል፤ እናንተም የምትሰጡት በግድ ሳይሆን በፈቃደኛነት መሆኑን ያሳያል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ስለ​ዚ​ህም አስ​ቀ​ድ​መው ወደ እና​ንተ መጥ​ተው በቅ​ድ​ሚያ የተ​ና​ገ​ራ​ች​ኋ​ትን በረ​ከ​ታ​ች​ሁን እን​ዲ​ያ​ዘ​ጋጁ ወን​ድ​ሞ​ችን ማለ​ድሁ፤ እን​ደ​ዚ​ህም የተ​ዘ​ጋጀ ይሁን፤ በረ​ከ​ትን እን​ደ​ም​ታ​ገ​ኙ​በት እንጂ በን​ጥ​ቂያ እንደ ተወ​ሰ​ደ​ባ​ችሁ አይ​ሁን።

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 9:5
11 交叉引用  

ይህችንም ያመጣሁልህን በረከቴን ተቀበል እግዚአብሔር በቸርነት ስጥቶኛልና ለእኔም ብዙ አለኝና። እስኪቀበለውም ድረስ ዘበዘበው።


እርሱም ከጭፍራው ሁሉ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመለሰ፤ መጥቶም በፊቱ ቆመና “እነሆ፥ ከእስራኤል ዘንድ በቀር በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ አወቅሁ፤ አሁንም ከባሪያህ ገጸ በረከት ትቀበል ዘንድ እለምንሃለሁ፤” አለ።


እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያን ጊዜ እንዳይሆን፥ ከእናንተ እያንዳንዱ በየሳምንቱ በፊተኛው ቀን እንደ ቀናው መጠን እያስቀረ በቤቱ ያስቀምጥ።


ስለዚህም ቲቶ አስቀድሞ እንደ ጀመረ እንዲሁ ደግሞ ይህን ቸር ሥራ ደግሞ በእናንተ ዘንድ ሊፈጽም ለመንን።


ነገር ግን ለእነርሱ እንዳልሁ፥ የተዘጋጃችሁ ትሆኑ ዘንድ በዚህም ነገር ስለ እናንተ ያለው ትምክህታችን ከንቱ እንዳይሆን ወንድሞችን እልካለሁ፤


ይህንም እላለሁ፦ በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል።


በስሌታችሁ የሚበዛውን ፍሬ እንጂ ስጦታውን ፈላጊ አይደለሁም።


እርስዋም፦ በረከትን ስጠኝ፥ በደቡብ በኩል ያለውን ምድር ሰጥተኸኛልና የውኃ ምንጭ ደግሞ ስጠኝ አለችው። ካሌብም ላይኛውንና ታችኛውን ምንጭ ሰጣት።


አሁንም ባሪያህ ወደ ጌታዬ ያመጣችው ይህ መተያያ ጌታዬን ለሚከተሉ ጕልማሶች ይሰጥ።


ዳዊትም ወደ ጺቅላግ በመጣ ጊዜ ለዘመዶቹ ለይሁዳ ሽማግሌዎች፦ እነሆ፥ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ምርኮ በረከትን ተቀበሉ ብሎ ከምርኮው ሰደደላቸው።


跟着我们:

广告


广告