Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 8:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አስቀድመውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን ለጌታ ለእኛም ሰጡ እንጂ እንዳሰብን አይደለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እኛ ከጠበቅነው በላይ፣ በመጀመሪያ ራሳቸውን ለጌታ ሰጡ፤ ቀጥለውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን ለእኛ ሰጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አስቀድመው ራሳቸውን ለጌታ ሰጡ፥ ከዚያም በእግዚአብሔር ፈቃድ ለእኛም ሰጡ፥ እንጂ እኛ አስበንበት ያደረግነው አይደለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እነርሱ ያደረጉት እኛ ከጠበቅነው በላይ ነው፤ በመጀመሪያ ራሳቸውን ለጌታ ሰጡ፤ ቀጥሎም በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን ለእኛ ሰጥተዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እነ​ርሱ አስ​ቀ​ድ​መው በፈ​ቃ​ዳ​ቸው፥ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ ለእ​ኛም አሳ​ል​ፈው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና እኛ እንደ አሰ​ብ​ነው አይ​ደ​ለም፤

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 8:5
15 交叉引用  

መንፈስም በሠላሳው አለቃ በዓማሣይ ላይ መጣ፤ እርሱም “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን፤” አለ። ዳዊትም ተቀበላቸው፤ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።


ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ፥ የእግዚአብሔር እጅ በይሁዳ ላይ ሆነ።


አባቶቻችሁም እንደ ነበሩ አንገተ ደንዳና አትሁኑ፤ እጃችሁንም ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ለዘላለም ወደ ተቀደሰው ወደ መቅደሱም ግቡ፤ ጽኑ ቍጣውም ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ።


ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፥ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።


ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፥ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፥ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፥ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።


እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።


ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።


በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ ጳውሎስ ወንድሙም ሶስቴንስ፥


ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን።


ወንድሞች ሆይ፥ ለመቄዶንያ አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ጸጋ እናስታውቃችኋለን፤


እግዚአብሔርም የለመንሁትን ልመናዬን ሰጥቶኛል፥ እኔም ደግሞ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፥ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告