Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 2:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ነገር ግን ዳግመኛ በኀዘን ወደ እናንተ እንዳልመጣ ስለ እኔ ቆረጥሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እንግዲህ ላሳዝናችሁ ስላልፈለግሁ ወደ እናንተ ዳግመኛ ላለመምጣት ወሰንሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ስለዚህ ዳግመኛ በጉብኝቴ እንዳላስቸግራችሁ ወደ እናንተ ላለመምጣት ቆረጥሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እንግዲህ እናንተን እንዳላሳዝናችሁ በማሰብ ለጒብኝት ወደ እናንተ ተመልሼ ላለመምጣት ቊርጥ ውሳኔ አደረግሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ግ​ዲህ እያ​ዘ​ንሁ ወደ እና​ንተ እን​ዳ​ል​መጣ በልቤ ይህን ወሰ​ንሁ።

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 2:1
13 交叉引用  

ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ፤


በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውሎና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቈረጠ።


በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይወስድ ዘንድ አሰበ፤


በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና።


ምን ትወዳላችሁ? በበትር ወይስ በፍቅርና በየውሃት መንፈስ ልምጣባችሁን?


እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ በሠራው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ እናንተና መንፈሴም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር ተሰብስበን፥


እኔ ግን ልራራላችሁ ስል እንደ ገና ወደ ቆሮንቶስ እንዳልመጣሁ በነፍሴ ላይ እግዚአብሔርን ምስክር እጠራለሁ።


ስለዚህ ጌታ ለማፍረስ ያይደለ ለማነጽ እንደ ሰጠኝ ሥልጣን፥ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በቁርጥ እንዳልሠራ በሩቅ ሆኜ ይህን እጽፋለሁ።


በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት በብዙም እንባ ጽፌላችሁ ነበርና፤ ይህም እናንተን አብዝቼ የምወድበትን ፍቅር እንድታውቁ እንጂ እንዳሳዝናችሁ አይደለም።


አርጢሞንን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ ስልክ፥ ወደ ኒቆጵልዮን ወደ እኔ እንድትመጣ ትጋ፤ በዚያ ልከርም ቍኦርጬአለሁና።


跟着我们:

广告


广告