Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ቆሮንቶስ 10:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በዓለማዊ ልማድ እንደምንመላለስ በሚቆጥሩን በአንዳንዶች ላይ አምኜ ልደፍር አስባለሁ፥ በዚያ እምነት ግን ከእናንተ ጋር ሆኜ እንዳልደፍር እለምንችኋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ፣ በዓለማዊ መንገድ እንደምንኖር አድርገው በሚቈጥሩን ሰዎች ላይ በድፍረት ለመናገር ቈርጫለሁ፤ እናንተን ግን በዚያ ዐይነት ድፍረት እንድናገር እንዳታደርጉኝ እለምናችኋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ስመጣ ግን በዓለማዊ ልማድ እንደምንመላለስ በሚቆጥሩን በአንዳንዶች ላይ በድፍረት ለመናገር አስባለሁ፤ እናንተን ግን በዚያ ድፍረት እንድናገር እንዳታደርጉኝ እለምናችኋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የምለምናችሁም ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ በድፍረት እንድናገር እንዳታደርጉኝ ነው፤ በሥጋ አስተሳሰብ እንደምንመላለስ አድርገው በሚገምቱን በአንዳንድ ሰዎች ፊት ግን በድፍረት ለመናገር እፈልጋለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ እሠ​ራ​ለሁ፤ በሥ​ጋዊ ሥር​ዐ​ትም እን​ደ​ም​ን​ኖር አድ​ር​ገው በሚ​ጠ​ረ​ጥ​ሩን ሰዎች ላይ በድ​ፍ​ረት ለመ​ና​ገር አስ​ባ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን በዚህ ዓይ​ነት ድፍ​ረት እን​ድ​ና​ገር እን​ዳ​ታ​ደ​ር​ጉኝ እለ​ም​ና​ች​ኋ​ለሁ።

参见章节 复制




2 ቆሮንቶስ 10:2
12 交叉引用  

እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።


እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ።


እንግዲህ ይህን ሳስብ ያን ጊዜ ቅሌትን አሳየሁን? ወይስ በእኔ ዘንድ አዎን አዎን አይደለም አይደለም ማለት እንዲሆን ያን የማስበው በዓለማዊ ልማድ ነውን?


ደካሞች መስለን እንደ ነበርን በውርደት እላለሁ። ነገር ግን በሞኝነት እላለሁ፤ ማንም በሚደፍርበት እኔ ደግሞ እደፍርበታለሁ።


ስለዚህ ጌታ ለማፍረስ ያይደለ ለማነጽ እንደ ሰጠኝ ሥልጣን፥ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በቁርጥ እንዳልሠራ በሩቅ ሆኜ ይህን እጽፋለሁ።


ሁለተኛ በእናንተ ዘንድ በነበርሁ ጊዜ እንደ ተናገርሁ አሁንም ደግሞ በሩቅ ስሆን፥ ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንዲናገር ማስረጃ ከፈለጋችሁ፥ እንደ ገና ብመጣ እንዳልራራላቸው አስቀድመው ኃጢአት ላደረጉት ለሌሎችም ሁሉ አስቀድሜ ብዬአለሁ፥ አስቀድሜም እላለሁ። ክርስቶስም ስለ እናንተ አይደክምም ነገር ግን በእናንተ ኃይለኛ ነው።


跟着我们:

广告


广告