Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 4:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ከፈሰሰም ናስ ከዳር እስከ ዳር ዐሥር ክንድ፥ ቁመቱም አምስት ክንድ፥ በዙሪያውም ሠላሳ ክንድ የሆነ ክብ ኵሬ ሠራ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እንዲሁም ስፋቱ ከጠርዝ እስከ ጠርዝ ዐሥር ክንድ፣ ቁመቱ ዐምስት ክንድ የሆነ ክብ ገንዳ ከቀለጠ ብረት ሠራ፤ ዙሪያውም ሲለካ ሠላሳ ክንድ ሆነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከቀለጠም ናስ ከዳር እስከ ዳር ዐሥር ክንድ፥ ቁመቱም አምስት ክንድ፥ ዙሪያውም ሠላሳ ክንድ የሆነ ክብ ኩሬ ሠራ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እንዲሁም ጥልቀቱ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር፥ የጐኑ አጋማሽ አራት ሜትር ከአርባ ሳንቲ ሜትር፥ ዙሪያው ዐሥራ ሦስት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር የሆነ ክብ ገንዳ አሠራ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ዳግ​መ​ኛም ከቀ​ለጠ ናስ ከዳር እስከ ዳር ዐሥር ክንድ፥ ቁመ​ት​ዋም አም​ስት ክንድ፥ ዙሪ​ያ​ዋም ሠላሳ ክንድ የሆነ ኵሬ ሠራ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 4:2
10 交叉引用  

እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁት። አለኝም፦ እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።


እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤


በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


ከለዳውያንም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የነበሩትን የናስ ዐምዶች፥ በእግዚአብሔርም ቤት የነበሩትን መቀመጫዎችና የናስ ኵሬ ሰባበሩ፤ ናሱንም ወደ ባቢሎን ወሰዱ።


በበታቹም ለአንድ ክንድ ዐሥር፥ ለአንድም ክንድ አሥር፥ ጕብጕቦች አዞረበት፤ ኵሬውም በቀለጠ ጊዜ ጕብጕቦቹ በሁለት ተራ ከእርሱ ጋር አብረው ቀልጠው ነበር።


የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥ ምንቸቶቹንም፥ መጫሪያዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ ሜንጦቹንም፥ ማንደጃዎቹንም አደረገ፤ ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አደረገ።


የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውንም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ከሚያገለግሉ ከሴቶች መስተዋት ከናስ አደረገ።


ከአድርአዛርም ከተሞች ከጢብሐትና ከኩን ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፤ ከዚህም ሰሎሞን የናሱን ኵሬና ዐምዶች የናሱንም ዕቃ ሠራ።


跟着我们:

广告


广告