Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 9:26 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ማልዶም ተነሡ፥ በነጋም ጊዜ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፦ ተነሣና ላስናብትህ አለው። ሳኦልም ተነሣ፥ እርሱና ሳሙኤልም ሁለቱ ወደ ሜዳ ወጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በማለዳ ተነሡ፤ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፣ “ላሰናብትህ ስለ ሆነ ተዘጋጅ” አለው። ሳኦልም ተዘጋጅቶ እንዳበቃ፣ ከሳሙኤል ጋራ ተያይዘው ወደ ውጭ ወጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በነጋም ጊዜ በማለዳ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፥ “ላሰናብትህ ስለሆነ ተዘጋጅ” አለው። ሳኦልም ተዘጋጅቶ እንዳበቃ፥ ከሳሙኤል ጋር ተያይዘው ወደ ውጭ ወጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በነጋም ጊዜ ማለዳ ሳሙኤል ከሰገነቱ ላይ ሳኦልን ጠርቶ “እንግዲህ ተነሥ፤ ላሰናብትህና መንገድህን ቀጥል” አለው፤ ሳኦልም ከመኝታው ተነሣ፤ እርሱና ሳሙኤልም አብረው ወደ መንገዱ ሄዱ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ በነ​ጋም ጊዜ ሳሙ​ኤል ሳኦ​ልን፥ “ከሰ​ገ​ነቱ ላይ ጠርቶ፦ ተነ​ሣና ላሰ​ና​ብ​ትህ” አለው። ሳኦ​ልም ተነሣ፤ እር​ሱና ሳሙ​ኤ​ልም ሁለቱ ወደ ሜዳ ወጡ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 9:26
6 交叉引用  

ሎጥ፥ ወጣ ልጆቹም ለሚያገቡት ለአማቶቹም ነገራቸው አላቸውም፥ ተነሡ ከዚህ ስፍራ ውጡ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋልና። ለአማቶቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው


ከከተማይቱም ወጥተው ገና ሳይርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ አለ፦ ተነሥተህ ሰዎቹና ተከተላቸው በደረስህባቸውም ጊዜ እንዲህ በላቸው፦ በመልካሙ ፋንታ፥


ተነሣና ሕዝቡን ቀድስ፥ እንዲህም በላቸው፦ እስራኤል ሆይ፥ እርም የሆነ ነገር በመካከልህ አለ፥ እርምም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም ብሎ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ተናግሮአልና እስከ ነገ ተቀደሱ።


እርሱም፦ ተነሺ፥ እንሂድ አላት፥ እርስዋ ግን ሞታ ነበርና አልመለሰችም፥ በዚያን ጊዜ በአህያው ላይ ጫናት፥ ተነሥቶም ወደ ስፍራው ሄደ።


ከኮረብታውም መስገጃ ወደ ከተማይቱ ወረዱ፥ ሳሙኤልም ለሳኦል በሰገነቱ ላይ መኝታ አዘጋጀለት፥ እርሱም ተኛ።


እነርሱም በከተማይቱ ዳር ሲወርዱ ሳሙኤል ሳኦልን፦ ብላቴናውን ወደ ፊታችን እንዲያልፍ እዘዘው፥ አንተ ግን የእግዚአብሔርን ቃል አሰማህ ዘንድ በዚህ ቁም አለው። ብላቴናውም አለፈ።


跟着我们:

广告


广告