Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 8:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ለራሱም የሻለቆችና የመቶ አለቆች ያደርጋቸዋል፥ እርሻውንም የሚያርሱ እህሉንም የሚያጭዱ የጦር መሣሪያውንና የሰረገሎቹንም ዕቃ የሚሠሩ ይሆናሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አንዳንዶቹን ሻለቆችና ዐምሳ አለቆች ያደርጋቸዋል፤ ሌሎቹን መሬቱን እንዲያርሱና እህሉን እንዲያጭዱ፣ የቀሩትን ደግሞ የጦር መሣሪያና ለሠረገላ የሚሆኑትን ዕቃዎች እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አንዳንዶቹን ሻለቆችና አምሳ አለቆች ያደርጋቸዋል፤ ሌሎቹን መሬቱን እንዲያርሱና እህሉን እንዲያጭዱ፥ ሌሎቹን ደግሞ የጦር መሣሪያና ለሠረገላ የሚሆኑትን ዕቃዎች እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከእነርሱም አንዳንዶቹን የሺህ አለቆችና የኀምሳ አለቆች አድርጎ ይሾማል፤ ወንዶቹ ልጆቻችሁ የንጉሡ ሁዳድ አራሾችና መከር ሰብሳቢዎች ይሆናሉ፤ ሌሎችም የጦር መሣሪያና የሠረገላ ዕቃ ሠራተኞች ይሆናሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ለራ​ሱም የሻ​ለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችም ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ እር​ሻ​ው​ንም የሚ​ያ​ርሱ፥ እህ​ሉ​ንም የሚ​ያ​ጭዱ፥ ፍሬ​ው​ንም የሚ​ለ​ቅሙ፥ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ው​ንና የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም ዕቃ የሚ​ሠሩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 8:12
8 交叉引用  

ለንጉሡና ለቤተ ሰቡም ቀለብ የሚሰጡ በእስራኤል ሁሉ ላይ ዐሥራ ሁለት ሹሞች ለሰሎሞን ነበሩት። ከዓመቱ ውስጥ አንዱን ወር እያንዳንዳቸው ይቀልቡ ነበር።


ሙሴም ከዘመቻ በተመለሱት በጭፍራ አለቆች፥ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ።


ሳኦልም በአጠገቡ የቆሙትን ባሪያዎቹን፦ ብንያማውያን ሆይ፥ እንግዲህ ስሙ፥ በውኑ የእሴይ ልጅ እርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁ ይሰጣችኋልን? ሁላችሁንስ ሻለቆችና የመቶ አለቆች ያደርጋችኋልን?


ሴቶች ልጆቻችሁንም ወስዶ ሽቶ ቀሚሚዎችና ወጥቤቶች አበዛዎችም ያደርጋቸዋል።


跟着我们:

广告


广告