Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ግብጻውያንና ፈርዖንም ልባቸውን እንዳጸኑ ልባችሁን ለምን ታጸናላችሁ? እግዚአብሔር ኃይሉን ካደረገባቸው በኋላ ያወጡአቸው አይደሉምን? እነርሱም አልሄዱምን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እንደ ግብጻውያንና እንደ ፈርዖን ልባችሁን የምታደነድኑት ለምንድን ነው? እነርሱም እስራኤላውያንን የለቀቋቸው እርሱ በጽኑ ከቀጣቸው በኋላ አይደለምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ግብፃውያንና ፈርዖን እንዳደረጉት ልባችሁን የምታደነድኑት ለምንድን ነው? እነርሱ እስራኤላውያንን የለቀቋቸው እርሱ በጽኑ ከቀጣቸው በኋላ አይደለምን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የግብጽ ንጉሥና ግብጻውያን እንዳደረጉት ስለምን ልባችሁን ታደነድናላችሁ? እስራኤላውያን የግብጽን ምድር ለቀው የወጡት፥ እግዚአብሔር ግብጻውያንን በብርቱ ከቀጣቸው በኋላ አልነበረምን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ግብ​ጻ​ው​ያ​ንና ፈር​ዖ​ንም ልባ​ቸ​ውን እን​ዳ​ጸኑ ልባ​ች​ሁን ለምን ታጸ​ና​ላ​ችሁ? በተ​ዘ​ባ​በ​ቱ​ባ​ቸው ጊዜ ያወ​ጡ​አ​ቸው አይ​ደ​ሉ​ምን? እነ​ር​ሱም አል​ሄ​ዱ​ምን?

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 6:6
16 交叉引用  

ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ ደፍሮትስ በደኅና የሄደ ማን ነው?


ሙሴም አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ አሉትም፤ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በፊቴ ለመዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ያገለግሉኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።


እነሆም እኔ የግብፃውያንን ልብ አጸናለሁ፤ በኋላቸውም ይገባሉ፤ በፈርዖንና በሠራዊቱም ሁሉ በሰረገሎቹም በፈረሰኞቹም ላይ ክብር አገኛለሁ።


ግብፃውያንም፥ የፈርዖን ፈረሶችና ሰረገሎች ፈረሰኞቹም ሁሉ፥ እያሳደዱ በኋላቸው ወደ ባሕር መካከል ገቡ።


እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ “ወደ ግብፅ ስትመለስ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራት ሁሉ በፈርዖን ፊት ታደርገው ዘንድ ተመልከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸናዋለሁ፤ ሕዝቡንም አይለቅቅም።


እግዚአብሔር እንደ ተናገረ፥ የፈርዖን ልብ ጸና፤ አልሰማቸውምም።


እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ “የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ።


ፈርዖንም ጸጥታ እንደሆነ ባየ ጊዜ ልቡን አደነደነ፤ እግዚአብሔርም እንደተናገረ አልሰማቸውም።


ፈርዖንም በዚህ ጊዜ ደግሞ ልቡን አደነደነ፤ ሕዝቡንም አልለቀቀም።


ነገር ግን ኃይሌን እገልጥብህ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ስለዚህ አስነሥቼሃለሁ።


ፈርዖንም ዝናቡ በረዶውም ነጎድጓዱም እንደ ተቍረጠ ባየ ጊዜ ኃጢያትን ጨመረ፤ እርሱና ባሪያዎቹም ልባቸውን አደነደኑ።


ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቍጣ ቀን ቍጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ።


ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤


跟着我们:

广告


广告