Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 6:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እነርሱም፦ ስለ በደል መሥዋዕት የምንመልስለት ምንድር ነው? አሉ። እነርሱም እንዲህ አሉ፦ እናንተንና አለቆቻችሁን ያገኘች መቅሠፍት አንዲት ናትና እንደ ፍልስጥኤማውያን አለቆች ቁጥር አምስት የወርቅ እባጮች አምስትም የወርቅ አይጦች አቅርቡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ፍልስጥኤማውያንም፣ “የምንልከው የበደል መሥዋዕት ምን መሆን አለበት?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተንም ሆነ አለቆቻችሁን የመታው መቅሠፍት አንድ ዐይነት በመሆኑ፣ በፍልስጥኤማውያን ገዦች ቍጥር ልክ ዐምስት የወርቅ ዕባጮችና ዐምስት የወርቅ ዐይጦች ላኩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እነርሱም፥ “የምንልከው የበደል መሥዋዕት ምን መሆን አለበት?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተንም ሆነ አለቆቻችሁን የመታው መቅሠፍት አንድ ዓይነት በመሆኑ፥ በፍልስጥኤማውያን ገዥዎች ቍጥር አምስት የወርቅ ዕባጮችና አምስት የወርቅ ዐይጦች ላኩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሕዝቡም፥ “ስለ በደል የሚከፈል ይሆን ዘንድ ከምን ዐይነት ስጦታ ጋር እንላከው?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “በእባጩ አምሳል የተሠራ አምስት የወርቅ ጒልቻ፥ እንደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ብዛት በአይጥ አምሳል የተሠራ አምስት የወርቅ ጉልቻ መሆን አለበት፤ በእናንተ ሁሉና በአምስቱ ገዢዎች ላይ የተላከው መቅሠፍት አንድ ዐይነት ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እነ​ር​ሱም፥ “ስለ መቅ​ሠ​ፍቱ የም​ን​ሰ​ጠው የበ​ደል መባእ ምን​ድን ነው?” አሉ። እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ፥ “እና​ን​ተ​ንና አለ​ቆ​ቻ​ች​ሁን፥ ሕዝ​ባ​ች​ሁ​ንም ያገ​ኘች መቅ​ሠ​ፍት አን​ዲት ናትና እንደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች ቍጥር አም​ስት የወ​ርቅ እባ​ጮች፥ አም​ስ​ትም የወ​ርቅ አይ​ጦች አቅ​ርቡ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 6:4
10 交叉引用  

የእስራኤልም ልጆች ሙሴ እንዳዘዘ አደረጉ፤ ከግብፃውያንም የብርንና የወርቅን ዕቃ ልብስንም ለመኑ።


በግብፅ ፊት ካለው ከሺሖር ወንዝ ጀምሮ በሰሜን በኩል እስካለችው የከነዓናውያን ሆና እስከ ተቈጠረችው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ፥ የጋዛ፥ የአዛጦን፥ የአስቀሎና፥ የጌት፥ የአቃሮን፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት፥


የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ በኃይል ወረደ፥ ወደ አስቀሎናም ወረደ፥ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፥ ልብሳቸውንም ወስዶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጠ። ቁጣውም ነደደ፥ ወደ አባቱም ቤት ወጣ።


አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት፥ ከነዓናውያንም ሁሉ፥ ሲዶናውያንም፥ ከበኣልአርሞንዔም ተራራ ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ በሊባኖስ ተራራ የሚኖሩትም ኤዊያውያን።


ያልሞቱትም ሰዎች በእባጭ ተመቱ፥ የከተማይቱም ዋይታ እስከ ሰማይ ወጣ።


የእግዚአብሔርም እጅ በአዛጦን ሰዎች ላይ ከበደች፥ አጠፋቸውም፥ አዛጦንንና ድንበራቸውንም በእባጭ መታቸው።


ከተሸከሙትም በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በታላቅ ድንጋጤ በከተማይቱ ላይ ሆነች፥ ከታናሹም እስከ ታላቁ ድረስ የከተማይቱን ሰዎች መታ፥ እባጭም መጣባቸው።


የእባጫችሁንም ምሳሌ ምድራችሁንም የሚያጠፋአትን የአይጦችን ምሳሌ አድርጋችሁ ለእስራኤል አምላክ ክብርን ስጡ፥ እጁን ከእናንተና ከአማልክቶቻችሁ ከምድራችሁም ምናልባት ያቀልል ይሆናል።


የእግዚአብሔርንም ታቦት ወስዳችሁ በሰረገላው ላይ አኑሩት፥ ስለ በደልም መሥዋዕት ያቀረባችሁትን የወርቁን ዕቃ በሣጥን ውስጥ አድርጋችሁ በታቦቱ አጠገብ አኑሩት፥ ይሄድም ዘንድ ስደዱት።


跟着我们:

广告


广告