Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 6:17 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ፍልስጥኤማውያን ስለ በደል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀረቡአቸው የወርቅ እባጮች እነዚህ ናቸው፥ አንዲቱ ለአዛጦን፥ አንዲቱም ለጋዛ፥ አንዲቱም ለአስቀሎና፥ አንዲቱ ለጌት፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ፍልስጥኤማውያን ስለ በደል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የላኳቸው የወርቅ ዕባጮች አንዱ ስለ አሽዶድ፣ አንዱ ስለ ጋዛ፣ አንዱ ስለ አስቀሎና፣ አንዱ ስለ ጋትና አንዱ ስለ አቃሮን የቀረቡ ናቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ፍልስጥኤማውያን ስለ በደል መሥዋዕት ለጌታ የላኳቸው የወርቅ ዕባጮች እነዚህ ናቸው፤ አንዱ ስለ አሽዶድ፥ አንዱ ስለ ጋዛ፥ አንዱ ስለ አስቀሎና፥ አንዱ ስለ ጌት፥ አንዱ ስለ ዔቅሮን የቀረቡ ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለ በደላቸው የሚከፈሉ ስጦታዎች ይሆኑ ዘንድ ፍልስጥኤማውያን ለእግዚአብሔር የላኩአቸው በእባጮች አምሳል የተሠሩ አምስት የወርቅ እንክብሎች አሽዶድ፥ ጋዛ፥ አስቀሎና፥ ጋትና ዔቅሮን ተብለው በሚጠሩት ከተሞቻቸው ስም የተላኩ ነበሩ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ስለ በደል መባእ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረ​ቡ​አ​ቸው የሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ምሳሌ የወ​ርቅ እባ​ጮች እነ​ዚህ ናቸው፦ አን​ዲቱ ለአ​ዛ​ጦን፥ አን​ዲ​ቱም ለጋዛ፥ አን​ዲ​ቱም ለአ​ስ​ቀ​ሎና፥ አን​ዲ​ቱም ለጌት፥ አን​ዲ​ቱም ለአ​ቃ​ሮን።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 6:17
19 交叉引用  

የፍልስጥኤማውያን ቈነጃጅት ደስ እንዳይላቸው፥ የቆላፋንም ቈነጃጅት እልል እንዳይሉ፥ በጌት ውስጥ አታውሩ፥ በአስቀሎናም አደባባይ የምስራች አትበሉ።


እነዚህም አራቱ በጌት ውስጥ ከራፋይም የተወለዱ ነበሩ፥ በዳዊትም እጅ በባሪያዎቹም እጅ ወደቀ።


አካዝያስም በሰማርያ በሰገነቱ ላይ ሳለ ከዐይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እርሱም “ሂዱ፤ ከዚህም ደዌ እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ፤” ብሎ መልእክተኞችን ላከ።


ወጥቶም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፤ የጌትንና የየብናን የአዞጦንንም ቅጥር አፈረሰ፤ በአዛጦንና በፍልስጥኤማውያንም አገር ከተሞችን ሠራ።


የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ አስቀሎናንም ጋዛንም አቃሮንንም የአዛጦንንም ቅሬታ፥


ስለ ሠራው ኃጢአት ለበደል መሥዋዕት ጠቦትን ለማምጣት ገንዘቡ ያልበቃ እንደ ሆነ፥ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእግዚአብሔር ያቀርባል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለኤዶምያስ አሳልፈው ይሰጡአቸው ዘንድ ምርኮኞችን ሁሉ ማርከዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጋዛ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።


ወደ ካልኔ አልፋችሁ ተመልከቱ፥ ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፥ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፥ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይሻላሉን? ወይስ ድንበራቸው ከድንበራችሁ ይሰፋልን?


እግዚአብሔር ፈውስ በሌለው በግብፅ ቁስል በእባጭም በቍቁቻም በችፌም ይመታሃል።


ይሁዳም ጋዛንና ዳርቻዋን፥ አስቀሎናንና ዳርቻዋን፥ አቃሮንንና ዳርቻዋን ያዘ።


የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ በኃይል ወረደ፥ ወደ አስቀሎናም ወረደ፥ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፥ ልብሳቸውንም ወስዶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጠ። ቁጣውም ነደደ፥ ወደ አባቱም ቤት ወጣ።


ሶምሶንም ወደ ጋዛ ሄደ፥ በዚያም ጋለሞታ ሴት አይቶ ወደ እርስዋ ገባ።


ፍልስጥኤማውያንም ይዘው ዓይኖቹን አወጡት፥ ወደ ጋዛም አምጥተው በናስ ሰንሰለት አሰሩት፥ በግዞትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር።


ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ወሰዱ፥ ከአቤንኤዘርም ወደ አዛጦን ይዘውት መጡ።


የእግዚአብሔርንም ታቦት ወደ አስቀሎና ሰደዱት። የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አስቀሎና በመጣ ጊዜ አስቀሎናውያን፦ እኛንና ሕዝባችንን ሊገድሉ የእስራኤልን አምላክ ታቦት አመጡብን ብለው ጮኹ።


ልከውም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ወደ እነርሱ ሰበሰቡና፦ በእስራኤል አምላክ ታቦት ምን እናድርግ? አሉ፥ እነርሱም፦ የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ ጌት ይዙር ብለው መለሱ። የእስራኤልንም አምላክ ታቦት ወደዚያ ተሸከሙት።


እነርሱም፦ ስለ በደል መሥዋዕት የምንመልስለት ምንድር ነው? አሉ። እነርሱም እንዲህ አሉ፦ እናንተንና አለቆቻችሁን ያገኘች መቅሠፍት አንዲት ናትና እንደ ፍልስጥኤማውያን አለቆች ቁጥር አምስት የወርቅ እባጮች አምስትም የወርቅ አይጦች አቅርቡ።


跟着我们:

广告


广告