Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 5:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ከተሸከሙትም በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በታላቅ ድንጋጤ በከተማይቱ ላይ ሆነች፥ ከታናሹም እስከ ታላቁ ድረስ የከተማይቱን ሰዎች መታ፥ እባጭም መጣባቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ነገር ግን ታቦቱን ወደዚያ ከወሰዱት በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፤ ታላቅ መሸበርም አመጣባቸው፤ ሕፃን ሽማግሌ ሳይል ሕዝቡን በዕባጭ መታ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ነገር ግን ታቦቱን ወደዚያ ከወሰዱትም በኋላ የጌታ እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፤ ታላቅ መሸበርም አመጣባቸው፤ ሕፃን ሽማግሌ ሳይል ሕዝቡን በእባጭ መቅሠፍት መታ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ነገር ግን የቃል ኪዳኑ ታቦት እዚያ ከደረሰ በኋላ እግዚአብሔር ያቺንም ከተማ ጭምር ቀጣ፤ ሕዝብዋንም በብርቱ አስጨነቀ። ሕፃኑንም ሽማግሌውንም ሳይለይ ሕዝቡን ሁሉ በአንድነት በእብጠት በሽታ ቀጣቸው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ከሄ​ደ​ችም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ላይ መጣች፤ ታላቅ ሁከ​ትም ሆነ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ሰዎች ታላ​ቁ​ንም ታና​ሹ​ንም መታ፤ የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ው​ንም በእ​ባጭ መታ​ቸው፤ የጌት ሰዎ​ችም የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ውን ምስል ሠሩ፥

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 5:9
11 交叉引用  

ከአንበሳ ፊት እንደ ሸሸ ድብም እንዳገኘው ሰው፥ ወይም ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ነው።


ከሰፈርም መካከል ተቈርጠው እስኪጠፉ ድረስ የእግዚአብሔር እጅ በላያቸው ነበረ።


ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰሙ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ብታምፁ፥ በእናንተና በንጉሣችሁ ላይ የእግዚአብሔር እጅ ትሆናለች።


የእግዚአብሔርንም ታቦት ወደ አስቀሎና ሰደዱት። የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አስቀሎና በመጣ ጊዜ አስቀሎናውያን፦ እኛንና ሕዝባችንን ሊገድሉ የእስራኤልን አምላክ ታቦት አመጡብን ብለው ጮኹ።


በከተማይቱ ሁሉ የሞት ድንጋጤ ነበርና፥ የእግዚአብሔርም እጅ በዚያ እጅግ ከብዳ ነበረችና ልከው የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ሰብስበው፦ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱ፥ እኛንና ሕዝባችንን እንዳይገድል ወደ ስፍራው ይመለስ አሉ።


የእግዚአብሔርም እጅ በአዛጦን ሰዎች ላይ ከበደች፥ አጠፋቸውም፥ አዛጦንንና ድንበራቸውንም በእባጭ መታቸው።


የእግዚአብሔርንም ታቦት፥ የወርቁ አይጦችና የእባጮቻቸው ምሳሌ ያሉበትንም ሣጥን በሰረገላው ላይ ጫኑ።


ፍልስጥኤማውያንም ተዋረዱ፥ ዳግመኛም ከዚያ ወዲያ ወደ እስራኤል ድንበር አልወጡም፥ በሳሙኤል ዕድሜ ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ነበረች።


跟着我们:

广告


广告