Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 5:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በነጋውም ማለዱ፥ እነሆም፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ ነበር፥ የዳጎንም ራስ እጆቹም ተቆርጠው በመድረኩ ላይ ወድቀው ነበር፥ የዳጎንም ደረት ብቻውን ቀርቶ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በሚቀጥለው ቀን ጧት ተነሥተው ሲመለከቱ፣ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት፣ መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ነበር፤ ራሱና እጆቹ ተሰባብረው በደጃፉ ላይ የወደቁ ሲሆን፣ የቀረው ሌላው አካሉ ብቻ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ነገር ግን በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ተነሥተው ሲመለከቱ፥ ዳጎን በጌታ ታቦት ፊት፥ መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ነበር፤ ራሱና እጆቹ ተሰባብረው በደጃፉ ላይ የወደቁ ሲሆኑ፥ የቀረው ሌላው አካሉ ብቻ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በተከታዩም ቀን ማለዳ ተነሥተው ሲመለከቱ የምስሉ ሐውልት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እንደገና ወድቆ አዩት፤ በዚህ ጊዜ ራሱና ሁለት እጆቹ ተሰባብረው በመግቢያው መድረክ ላይ ወድቀው ሌላው አካሉ ብቻ ቀርቶ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በነ​ጋ​ውም ማለዱ፤ እነ​ሆም፥ ዳጎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ነበር፤ የዳ​ጎ​ንም ራስ፥ ሁለቱ እጆ​ቹም ተቈ​ር​ጠው እየ​ራ​ሳ​ቸው በመ​ድ​ረኩ ላይ ወድ​ቀው ነበር፤ ሁለቱ መሀል እጆ​ቹም በወ​ለሉ ላይ ወድ​ቀው ነበር። የዳ​ጎ​ንም ደረት ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 5:4
11 交叉引用  

ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፥ ይህም ኃጢአትን የማስወገድ ፍሬ ሁሉ ነው።


ለዚህ መባዕ ገንዘቡ ያልበቃው ድሀ የማይነቅዘውን እንጨት ይመርጣል፥ ምስሉም እንዳይናወጥ ያቆመው ዘንድ ብልህ ሠራተኛን ይፈልጋል።


እናንተም፦ ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ ትሉአቸዋላችሁ።


ሰው ሁሉ እውቀት አጥቶ ሰንፎአል፥ አንጥረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል፥ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስትንፋስም የላቸውምና።


እነርሱ ምናምንቴና የቀልድ ሥራ ናቸው፥ በተጐበኙ ጊዜ ይጠፋሉ።


በአሕዛብ መካከል ተናገሩ አውሩም፥ ዓላማውንም አንሡ፥ አውሩ፥ አትደብቁ፦ ባቢሎን ተወሰደች፥ ቤል አፈረ፥ ሜሮዳክ ደነገጠ፥ ምስሎችዋ አፈሩ፥ ጣዖታትዋ ደነገጡ በሉ።


አማልክቶቻቸውንና ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎቻቸውን ከብርና ከወርቅም የተሠሩትን የከበሩትን ዕቃዎች ወደ ግብጽ ይማርካል፥ እስከ ጥቂትም ዓመት ድረስ ከሰሜን ንጉሥ ጋር ሳይዋጋ ይቀመጣል።


የተቀረጹትም ምስሎችዋ ይደቅቃሉ፥ በግልሙትና ያገኘችው ዋጋ ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፥ ጣዖታትዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፥ በግልሙትና ዋጋ ሰበሰባቻቸው፥ ወደ ግልሙትናም ዋጋ ይመለሳሉና።


የእባጫችሁንም ምሳሌ ምድራችሁንም የሚያጠፋአትን የአይጦችን ምሳሌ አድርጋችሁ ለእስራኤል አምላክ ክብርን ስጡ፥ እጁን ከእናንተና ከአማልክቶቻችሁ ከምድራችሁም ምናልባት ያቀልል ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告