Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 4:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ምራቱም የፊንሐስ ሚስት አርግዛ ልትወልድ ተቃርባ ነበር፥ የእግዚአብሔርም ታቦት እንደ ተማረከች፥ አማትዋና ባልዋም እንደ ሞቱ በሰማች ጊዜ ምጥ ደርሶባት ነበርና ተንበርክካ ወለደች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በዚያ ጊዜ ምራቱ የፊንሐስ ሚስት፣ ነፍሰ ጡር ነበረች፤ የምትወልድበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር፣ የእግዚአብሔርን ታቦት መማረክ፣ የዐማቷንና የባሏንም መሞት በሰማች ጊዜ ምጡ ስለ ጠናባት ተንበርክካ ወለደች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በዚያን ጊዜ ምራቱ የፊንሐስ ሚስት፥ ነፍሰ ጡር ነበረች፤ የምትወልድበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር፥ የእግዚአብሔርን ታቦት መማረክ፥ የዐማቷንና የባሏንም መሞት በሰማች ጊዜ ምጡ ስለ ጠናባት ተንበርክካ ወለደች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የፊንሐስ ሚስት የነበረችው የዔሊ ምራት ነፍሰ ጡር ነበረች፤ የምትወልድበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት መማረኩን፤ ዐማትዋና ባልዋ መሞታቸውን በሰማች ጊዜ በድንገተኛ ምጥ ተይዛ ወለደች፤ ምጡም ጸንቶባት ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ምራ​ቱም የፊ​ን​ሐስ ሚስት አር​ግዛ ልት​ወ​ልድ ተቃ​ርባ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት እንደ ተማ​ረ​ከች፥ አማ​ቷና ባል​ዋም እንደ ሞቱ በሰ​ማች ጊዜ አለ​ቀ​ሰች፤ ከዚ​ያም በኋላ ወለ​ደች። ሕማ​ም​ዋም ተመ​ለ​ሰ​ባት።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 4:19
7 交叉引用  

ለሴቲቱም አለ፤ በፀነሰሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።


ምጡም ባስጨነቅስት ጊዜ አዋላጂቱ፦ አትፍሪ ይኸኛው ደግሞ ወንድ ልጅ ይሆንሻልና አለቻት።


በዚያም ወራት የኢዮርብዓም ልጅ አብያ ታመመ።


ይህን ቤት እንደ ሴሎ አደርገዋለሁ፥ ይህችንም ከተማ ለምድር አሕዛብ ሁሉ እርግማን አደርጋታለሁ።


ሰውዮውም ስለ እግዚአብሔር ታቦት በተናገረ ጊዜ ዔሊ በበሩ አጠገብ ካለው ከወንበሩ ወደቀ፥ እርሱ ሸምግሎ ደንግዞም ነበርና አንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱም በእስራኤል ላይ አርባ ዓመት ፈራጅ ነበረ።


ወደ ሞትም በቀረበች ጊዜ በዙሪያዋ ያሉት ሴቶች፦ ወንድ ልጅ ወልደሻልና አትፍሪ አሉአት። እርስዋ ግን አልመለሰችላቸውም፥ በልብዋም አላኖረችውም።


跟着我们:

广告


广告