1 ሳሙኤል 4:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 እስራኤልም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ በአቤንኤዘር አጠገብ ሰፈሩ፥ ፍልስጥኤማውያንም በአፌቅ ሰፈሩ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 የሳሙኤልም ቃል ወደ እስራኤል ሁሉ ደረሰ። በዚያ ዘመን እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ሊወጉ ወጡ፤ እስራኤላውያን በአቤንኤዘር፣ ፍልስጥኤማውያን ደግሞ በአፌቅ ሰፈሩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 የሳሙኤልም ቃል ወደ እስራኤል ሁሉ ደረሰ። በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ሊወጉ ወጡ፤ እነርሱ በአቤንኤዘር ሲሰፍሩ፥ ፍልስጥኤማውያን ደግሞ በአፌቅ ሰፈሩ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ወጡ፤ ስለዚህም እስራኤላውያን አቤንዔዜር ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንም አፌቅ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ሰፈሩ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 በእነዚያም ወራት እንዲህ ሆነ። ፍልስጥኤማውያን ለጦርነት በእስራኤላውያን ላይ ተሰበሰቡ። እስራኤልም ሊዋጉአቸው ወጡ፤ በአቤኔዜር አጠገብም ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንም በአፌቅ ሰፈሩ። 参见章节 |