Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 31:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የጦር ዕቃውንም በአስታሮት መቅደስ ውስጥ አኖሩት፥ ሬሳውንም በቤትሳን ቅጥር ላይ አንጠለጠሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የጦር መሣሪያውን በአስታሮት ቤተ ጣዖት ውስጥ አስቀመጡት፤ ሬሳውን ደግሞ በቤትሳን ግንብ ላይ አንጠለጠሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የጦር መሣሪያውን በአስታሮት ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖሩት፤ ሬሳውን ደግሞ በቤት ሻን ግንብ ላይ አንጠለጠሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከዚህ በኋላ ፍልስጥኤማውያን የሳኦልን የጦር መሣሪያዎች ዐስታሮት ተብላ በምትጠራው ሴት አምላካቸው ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖሩ። የሳኦልንም ሬሳ ቤትሻን ተብላ በምትጠራው ከተማ ቅጽር ግንብ ላይ በምስማር ቸነከሩት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የጦር መሣ​ሪ​ያ​ው​ንም በአ​ስ​ታ​ሮት መቅ​ደስ ውስጥ አኖ​ሩት። ሬሳ​ው​ንም በቤ​ት​ሶም ቅጥር ላይ አን​ጠ​ለ​ጠ​ሉት።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 31:10
7 交叉引用  

በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤትሳንና መንደሮችዋ ይብልዓምና መንደሮችዋ፥ ዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ዓይነዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ታዕናክና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ መጊዶና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ሦስቱ ኮረብቶች ለምናሴ ነበሩ።


ምናሴም የቤትሳንንና የመንደሮችዋን፥ የታዕናክንና የመንደሮችዋን፥ የዶርንና የመንደሮችዋን፥ የይብለዓምንና የመንደሮችዋን፥ የመጊዶንና የመንደሮችዋን ሰዎች አላወጣቸውም፥ ነገር ግን ከነዓናውያን በዚያ አገር በመቀመጥ ጸኑ።


እግዚአብሔርንም ትተው በኣልንና አስታሮትን አመለኩ።


ካህኑም፦ በኤላ ሸለቆ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ፥ እነሆ፥ በመጎናጸፊያ ተጠቅልሎ ከዚህ ከኤፉዱ በኋላ አለ፥ ትወድደውም እንደ ሆነ ውሰደው፥ ሌላ ከዚህ የለም አለ። ዳዊትም፦ እንደ እርሱ ያለ የለምና እርሱን ስጠኝ አለው።


ጀግኖች ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሁሉ ሄዱ፥ የሳኦልንም ሬሳ የልጆቹንም ሬሳ ከቤትሳን ቅጥር ላይ አወረዱ፥ ወደ ኢያቢስም መጡ፥ በዚያም አቃጠሉት።


ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፦ በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ እግዚአብሔር አቅኑ፥ እርሱንም ብቻ አምልኩ፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ያድናችኋል ብሎ ተናገራቸው።


跟着我们:

广告


广告