Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 30:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ዳዊትም፦ የእነዚህን ሠራዊት ፍለጋ ልከተልን? አገኛቸዋለሁን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እርሱም፦ ታገኛቸዋለህና፥ ፈጽመህም ምርኮውን ትመልሳለህና ፍለጋቸውን ተከተል ብሎ መለሰለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ዳዊትም፣ “ይህን ወራሪ ሰራዊት ልከተለውን? እደርስባቸዋለሁን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “በርግጥ ትደርስባቸዋለህ፤ ምርኮውንም ትመልሳለህ፤ ተከተል” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ዳዊትም፥ “ይህን ወራሪ ሠራዊት ልከተለውን? እደርስባቸዋለሁን?” ሲል ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “በእርግጥ ትደርስባቸዋለህ፤ ምርኮውንም ትመልሳለህ፤ ተከተላቸው!” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ዳዊትም “እነዚያን ወራሪዎች ተከታትዬ በማሳደድ ልያዛቸውን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “ተከተላቸው! እነርሱንም ይዘህ ምርኮኞችን በመታደግ ታድናለህ” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዳዊ​ትም፥ “የእ​ነ​ዚ​ህን ሠራ​ዊት ፍለጋ ልከ​ተ​ልን? አገ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ሁን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እር​ሱም፥ “ታገ​ኛ​ቸ​ዋ​ለ​ህና፥ ፈጽ​መ​ህም ምር​ኮ​ኞ​ቹን ታድ​ና​ለ​ህና ፍለ​ጋ​ቸ​ውን ተከ​ተል” ብሎ መለ​ሰ​ለት።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 30:8
21 交叉引用  

ከብቱንም ሁሉ አስመለሰ፥ ደግሞም ወንድሙን ሎጥንና ከብቶቹን ሴቶችንና ሕዝቡን ደግሞ መለሰ።


ዳዊትም፦ ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ፍልስጥኤማውያንን በእርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ አለው።


ዳዊትም እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እርሱም፦ በኋላቸው ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ አትውጣ።


ጠላትም፥ ‘አሳድጄ እይዛቸዋለሁ፤ ምርኮም እካፈላለሁ፤ ነፍሴም ትጠግባቸዋለች፤ ሰይፌንም እመዝዛለሁ፤ እጄም ታጠፋቸዋለች’ አለ።


በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ።


የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፥ እግዚአብሔርንም፦ የብንያምን ልጆች ለመውጋት አስቀድሞ ማን ይውጣልን? ብለው ጠየቁት፥ እግዚአብሔርም፦ ይሁዳ ይቅደም አለ።


የእስራኤልም ልጆች ወጥተው በእግዚአብሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለቀሱ፥ እግዚአብሔርንም፦ ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንቀርባለን? ብለው ጠየቁ። እግዚአብሔርም፦ በእነርሱ ላይ ውጡ አለ።


ጌዴዎንም ከሦስቱ መቶ ሰዎች ጋር ወደ ዮርዳኖስ ደርሶ ተሻገረ፥ ምንም እንኳ ቢደክሙ ያሳድዱ ነበር።


ከእግዚአብሔርም፦ ገና ወደዚህ የሚመጣ ሰው አለን? ብለው ደግሞ ጠየቁት እግዚአብሔርም፦ እነሆ፥ በዕቃ መካከል ተሸሽጎአል ብሎ መለሰ።


ሳኦልም፦ ፍልስጥኤማውያንን ልከተልን? በእስራኤልስ እጅ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀው። በዚያ ቀን ግን አልመለሰለትም።


ዳዊትም፦ ልሂድን? እነዚህንስ ፍልስጥኤማውያን ልምታን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ሂድ፥ ፍልስጥኤማውያንን ምታ ቅዒላንም አድን አለው።


ዳዊትም ደግሞ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም መልሶ፦ ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለሁና ተነሥተህ ወደ ቅዒላ ውረድ አለው።


ሳኦልም እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም በሕልም ወይም በኡሪም ወይም በነቢያት አልመለሰለትም።


ዳዊትም አማሌቃውያን የወሰዱትን ሁሉ አስጣላቸው፥ ሁለቱንም ሚስቶቹን አዳነ።


ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች፥ ከወሰዱትም ምርኮ ሁሉ፥ ታላቅም ሆነ ታናሽም ሆነ፥ ምንም የጎደለባቸው የለም፥ ዳዊትም ሁሉን አስጣለ።


跟着我们:

广告


广告