Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 29:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን ተቆጥተው፦ ይህ ሰው ባስቀመጥኸው ስፍራ ይቀመጥ ዘንድ ይመለስ፥ በሰልፍ ውስጥ ጠላት እንዳይሆነን ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይውረድ፥ ከጌታው ጋር በምን ይታረቃል? የእነዚህን ሰዎች ራስ በመቁረጥ አይደለምን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የፍልስጥኤማውያን አዛዦች ግን በአንኩስ ላይ ተቈጥተው እንዲህ አሉ፤ “ይህን ሰው ወደዚያው ወደ ሰጠኸው ቦታ ይመለስ ዘንድ ስደደው፤ በውጊያው ጊዜ በእኛ ላይ ተመልሶ ጠላት እንዳይሆን፣ ዐብሮን ወደ ጦርነቱ መሄድ የለበትም፤ የእኛን ሰዎች ራስ ቈርጦ ካልወሰደ ከጌታው ጋራ እንዴት ሊታረቅ ይችላል?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የፍልስጥኤማውያን አዛዦች ግን በአኪሽ ላይ ተቆጥተው እንዲህ አሉ፤ “ይህን ሰው እንዲመለስ አድርግ፤ ወደ ሰጠኸው ቦታ ይመለስ ዘንድ ስደደው፤ በውጊያው ላይ ተመልሶ ጠላት እንዳይሆን ከእኛ ጋር አይወርድም። እዚህ ያሉትን የእኛን ሰዎች ራስ ቆርጦ ካልወሰደ በስተቀር፥ ከጌታው ጋር እንዴት ሊታረቅ ይችላል?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ነገር ግን የፍልስጥኤም ጦር አዛዦች በአኪሽ ላይ ተቈጥተው እንዲህ አሉት፤ “ይህን ሰው ቀድሞ ወደ ሰጠኸው ከተማ መልሰው፤ ከእኛ ጋር አብሮ እንዲዘምት አታድርግ፤ ጦርነቱ በሚፋፋምበት ወቅት በእኛ ላይ ሊነሣ ይችላል፤ እርሱ ከጌታው ጋር ለመስማማት የእኛን ሰዎች ከመግደል ሌላ ምን አማራጭ ይኖረዋል?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች ግን በእ​ርሱ ላይ ተቈ​ጥ​ተው፥ “ይህን ሰው ወደ አመ​ጣ​ህ​በት ቦታ መል​ሰው፤ በሰ​ል​ፉም ውስጥ ጠላት እን​ዳ​ይ​ሆ​ነን ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይ​ው​ረድ፤ ከጌ​ታው ጋር በምን ይታ​ረ​ቃል? የእ​ነ​ዚ​ህን ሰዎች ራስ በመ​ቍ​ረጥ አይ​ደ​ለ​ምን?

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 29:4
8 交叉引用  

ዳዊትም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሳኦልን ሊወጋ በመጣ ጊዜ ከምናሴ ወገን ሰዎች ወደ ዳዊት ከዱ፤ የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን “በራሳችን ላይ ጕዳት አድርጎ ወደ ጌታው ወደ ሳኦል ይመለሳል፤” ሲሉ ተማክረው ሰድደውታልና እነርሱ አልረዱአቸውም።


ወደ ጺቅላግም ሲሄድ ከምናሴ ወገን የምናሴ ሻለቆች የነበሩ ዓድና፥ ዮዛባት፥ ይዲኤል፥ ሚካኤል፥ ዮዛባት፥ ኤሊሁ፥ ጺልታይ ወደ እርሱ ከዱ።


እንዳይበዙ፥ ሰልፍም በተነሳብን ጊዜ ጠላቶቻችንን አግዘው እንዳይወጉን ከምድሪቱም እንዳይወጡ፥ ኑ! እንጠበብባቸው፤” አለ።


ጌታውም ዓመፀኛውን መጋቢ በልባምነት ስላደረገ አመሰገነው የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ልባሞች ናቸውና።


ቀድሞ ከፍልስጥኤማውያን ጋር የነበሩት ከእነርሱም ጋር ከሰፈሩ ዙሪያ የወጡት ዕብራውያን ደግሞ ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ወደ ነበሩት እስራኤላውያን ለመሆን ዞሩ።


በዚያም ቀን አንኩስ ጺቅላግን ሰጠው፥ ስለዚህም ጺቅላግ እስከ ዛሬ ድረስ ለይሁዳ ነገሥታት ሆነች።


አንኩስም መልሶ ዳዊትን፦ እንደ አምላክ መልእክተኛ በዓይኔ ፊት መልካም እንደ ሆንህ አውቃለሁ፥ ነገር ግን የፍልስጥኤማውያን አለቆች፦ ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይወጣም አሉ።


እንዲህም ሆነ፥ ዳዊትና ሰዎቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ጺቅላግ በመጡ ጊዜ፥ አማሌቃውያን በደቡብ አገርና በጺቅላግ ላይ ዘምተው ነበር፥ ጺቅላግንም መትተው በእሳት አቃጥለዋት ነበር፥


跟着我们:

广告


广告