Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 28:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሳሙኤል ግን ሞቶ ነበር፥ እስራኤልም ሁሉ አልቅሰውለት ነበር፥ በከተማውም በአርማቴም ቀብረውት ነበር። ሳኦልም መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድር አጥፍቶ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሞቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም ሁሉ በገዛ ከተማው በአርማቴም አልቅሰው ቀበሩት። ሳኦል ሙታን ሳቢዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን ከምድሪቱ አባርሯቸው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሞቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም ሁሉ በገዛ ከተማው በራማ አልቅሰው ቀበሩት። ሳኦልም ሙታን ሳቢዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን ከምድሪቱ አባሯቸው ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እነሆ፥ ሳሙኤል ከሞተ ቈየት ብሎአል፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ለእርሱ በማዘን አልቅሰው በሚኖርባት በራማ ቀብረውታል፤ ቀደም ሲል ሳኦል ጠንቋዮችንና ሙታን ጠሪዎችን ከእስራኤል ምድር እንዲባረሩ አስገድዶአቸው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሳሙ​ኤል ግን ሞቶ ነበር፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አል​ቅ​ሰ​ው​ለት ነበር፤ በከ​ተ​ማ​ውም በአ​ር​ማ​ቴም ቀብ​ረ​ውት ነበር። ሳኦ​ልም መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ከም​ድር አጥ​ፍቶ ነበር።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 28:3
12 交叉引用  

አባትዋም እርስዋን እንዳይሰጠው ፈጽሞ እንቢ ቢል እንደ ደናግል ማጫ ያህል ብር ይክፈላት።


መተተኛይቱን በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድላት።


ወደ መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቍዮች አትሂዱ፤ እንዳትረክሱባቸውም አትፈልጉአቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።


ሰው ወይም ሴት መናፍስት ቢጠሩ ወይም ጠንቍዮች ቢሆኑ ፈጸመው ይገደሉ፤ በድንጋይ ይውገሩአቸው፤ ደማቸው በላያቸው ነው።


መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቍዮችንም በሚከተል፥ በሥራቸውም በሚያመነዝር፥ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።


ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው፥ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ።


ሳሙኤልም ሞተ፥ እስራኤልም ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፥ በአርማቴምም በቤቱ ቀበሩት። ዳዊትም ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ።


ሴቲቱም፦ እነሆ፥ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድር እንዳጠፋ ሳኦል ያደረገውን ታውቃለህ፥ ስለ ምን እኔን ለማስገደል ወጥመድ ለነፍሴ ታደርጋለህ? አለችው።


ቤቱም በዚያ ነበረና ወደ አርማቴም ይመለስ ነበር፥ በዚያም በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።


跟着我们:

广告


广告