Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 28:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሳሙኤልም ሳኦልን፦ ለምን አወክኽኝ? ለምንስ አስነሣኸኝ? አለው። ሳኦልም መልሶ፦ ፍልስጥኤማውያን ይወጉኛልና እጅግ ተጨንቄአለሁ፥ እግዚአብሔርም ከእኔ ርቆአል፥ በነቢያት ወይም በሕልም አልመለሰልኝም፥ ስለዚህም የማደርገውን ታስታውቀኝ ዘንድ ጠራሁህ አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሳሙኤልም ሳኦልን፣ “አስነሥተህ የምታውከኝ ለምንድን ነው?” አለው። ሳኦልም፣ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ፍልስጥኤማውያን እየወጉኝ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእኔ ርቋል፤ በነቢያትም ሆነ በሕልም አልመለሰልኝም፤ ስለዚህ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ እንድትነግረኝ ጠራሁህ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “አስነሥተህ የምታውከኝ ለምንድነው?” አለው፤ ሳኦልም፥ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ፍልስጥኤማውያን እየወጉኝ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእኔ ርቋል፤ በነቢያትም ሆነ በሕልም አልመለሰልኝም፤ ስለዚህ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ እንድትነግረኝ ጠራሁህ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሳሙኤልም ሳኦልን “ዕረፍት የምትነሣኝ ስለምንድን ነው? ስለምንስ ከመቃብር እንድነሣ አስጠራኸኝ?” አለው። ሳኦልም “እነሆ፥ እኔ በታላቅ ችግር ላይ ነኝ! ፍልስጥኤማውያን ከእኔ ጋር ጦርነት በማድረግ ላይ ናቸው፤ እግዚአብሔርም እኔን ትቶኛል፤ በነቢይም ሆነ በሕልም መልስ ሊሰጠኝ አልፈለገም፤ ስለዚህም ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ትነግረኝ ዘንድ እንድትነሣ አስጠራሁህ” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “ለምን አወ​ክ​ኸኝ? ለም​ንስ አስ​ነ​ሣ​ኸኝ?” አለው። ሳኦ​ልም መልሶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ይወ​ጉ​ኛ​ልና እጅግ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእኔ ርቆ​አል፤ በነ​ቢ​ያት ወይም በሕ​ልም አላ​ሚ​ዎች አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም፤ ስለ​ዚ​ህም የማ​ደ​ር​ገ​ውን ታስ​ታ​ው​ቀኝ ዘንድ ጠራ​ሁህ” አለው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 28:15
18 交叉引用  

ልጆቻቸውንም ቢያሳድጉ ሰው እንዳይቀርላቸው ልጅ አልባ አደረጋቸዋለሁ፥ ከእነርሱም በራቅሁ ጊዜ ወዮላቸው!


በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።


እርስዋም፦ ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። ከእንቅልፉም ነቅቶ፦ እወጣለሁ እንደ ወትሮውም ጊዜ አደርጋለሁ አለ። ነገር ግን እግዚአብሔር ከእርሱ እንደ ተለየው አላወቀም።


እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ ከሳኦልም ስለ ተለየ ሳኦል ዳዊትን ፈራው።


ዳዊትም፦ ልሂድን? እነዚህንስ ፍልስጥኤማውያን ልምታን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ሂድ፥ ፍልስጥኤማውያንን ምታ ቅዒላንም አድን አለው።


ዳዊትም ደግሞ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም መልሶ፦ ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለሁና ተነሥተህ ወደ ቅዒላ ውረድ አለው።


ሴቲቱም፦ ማንን ላስነሣልህ? አለች፥ እርሱም፦ ሳሙኤልን አስነሽልኝ አለ።


ሳሙኤልም አለ፦ እግዚአብሔር ከራቀህ ጠላትም ከሆነህ ለምን ትጠይቀኛለህ?


ሳኦልም እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም በሕልም ወይም በኡሪም ወይም በነቢያት አልመለሰለትም።


ሳኦልም መልኩን ለውጦ ሌላ ልብስም ለብሶ ሄደ፥ ሁለትም ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ፥ በሌሊትም ወደ ሴቲቱ መጡ። እርሱም፦ እባክሽ፥ በመናፍስት አምዋርቺልኝ፥ የምልሽንም አስነሽልኝ አላት።


ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻቸው የሕዝቡ ሁሉ ልብ ተቆጥቶ ነበርና ሕዝቡ ሊወግሩት ስለ ተናገሩ ዳዊት እጅግ ተጨነቀ፥ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አበረታ።


跟着我们:

广告


广告