Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 27:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አንኩስም፦ በሕዝቡ በእስራኤል ዘንድ እጅግ የተጠላ ሆኖአል፥ ሰለዚህም ለዘላለም ባሪያ ይሆነኛል ብሎ ዳዊትን አመነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አንኩስም በልቡ፣ “እርሱ ራሱ የገዛ ሕዝቡ የሆኑት እስራኤላውያን እጅግ እንዲጠሉት ስላደረገ፣ ለዘላለም አገልጋዬ ይሆናል” ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አኪሽም በልቡ፥ “እርሱ ራሱ የገዛ ሕዝቡ የሆኑት እስራኤላውያን እጅግ እንዲጠሉት ስላደረገ፥ ለዘለዓለም አገልጋዬ ይሆናል” ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አኪሽ ግን ዳዊትን ስለሚተማመንበት በልቡ “በወገኖቹ በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ የተጠላ ስለ ሆነ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ያገለግለኛል” በማለት ያስብ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አን​ኩ​ስም፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እጅግ የተ​ጠላ ሆኖ​አል፤ ስለ​ዚ​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባሪያ ይሆ​ነ​ኛል” ብሎ ዳዊ​ትን አመ​ነው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 27:12
6 交叉引用  

ያዕቆብም ሌዊንና ስሞዖንን እንዲህ አለ፦ በዚች አገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ሰዎች የተጠላሁ ታደርጉኝ ዘንድ እኔን አስጨነቃችሁኝ እኔ በቁጥር ጥቂት ነኝ እነርሱ በእኔ ላይ ይስበሰቡና ይመቱኛል እኔም ከወገኔ ጋር እጠፋለሁ


የአሞን ልጆች በዳዊት ዘንድ እንደተጠሉ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከሶርያውያን ከቤትሮዖብና ከሱባ ሀያ ሺህ እግረኞች፥ ከመዓካ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎች፥ ከጦብም አሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ቀጠሩ።


እነርሱም፦ “በፈርዖንና በባሪያዎቹ ፊት ሽታችንን አግምታችሁታልና፥ ይገድሉንም ዘንድ ሰይፍን በእጃቸው ሰጥታችኋቸዋልና እግዚአብሔር ይመልከታችሁ፤ ይፍረድባችሁም፤” አሉአቸው።


እስራኤልም ሁሉ ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ እንደ መታ፥ ደግሞም እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ዘንድ እንደ ተጸየፉ ሰሙ፥ ሕዝቡም ሳኦልን ለመከተል ወደ ጌልገላ ተሰበሰቡ።


ዳዊት እንዲህ አደረገ በፍልስጥኤማውያንም አገር በሚቀመጥበት ዘመን ሁሉ ልማዱ ይህ ነበረ ብለው እንዳይናገሩብን ብሎ ዳዊት ወደ ጌት ያመጣቸው ዘንድ ወንድም ሆነ ሴትም ሆነ ማንንም በሕይወት አልተወም።


እንዲህም ሆነ፥ በዚያ ወራት ከእስራኤል ጋር ይዋጉ ዘንድ ፍልስጥኤማውያን ጭፍሮቻቸውን ለሰልፍ ሰበሰቡ፥ አንኩስም ዳዊትን፦ አንተና ሰዎችህ ከእኔ ጋር ወደ ሰልፍ እንድትወጡ በእርግጥ እወቅ አለው።


跟着我们:

广告


广告