Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 26:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ መጣ፥ ሳኦልና የሠራዊቱ አለቃ የኔር ልጅ አበኔርም የተኙበትን ስፍራ አየ፥ ሳኦልም በሰፈሩ ውስጥ ተኝቶ ነበር፥ ሕዝቡም በዙሪያው ሰፍሮ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልና የሰራዊቱ አለቃ፣ የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትን ስፍራ አየ። ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ሳለ፣ ሰራዊቱ በዙሪያው ሰፍሮ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልና የሠራዊቱ አለቃ፥ የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትን ስፍራ አየ። ሠራዊቱ በዙሪያው ሰፍሮ፥ ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከዚያም በፍጥነት ተነሥቶ በመሄድ ሳኦልና የሠራዊቱ አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር የሚተኙበትን ቦታ አረጋገጠ፤ ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ሳለ ወታደሮቹ በዙሪያው ይገኙ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዳዊ​ትም በቀ​ስታ ተነ​ሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈ​ረ​በት ቦታ መጣ፤ ሳኦ​ልና የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ የኔር ልጅ አቤ​ኔ​ርም የተ​ኙ​በ​ትን ስፍራ አየ፤ ሳኦ​ልም በድ​ን​ኳን ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ ሕዝ​ቡም በዙ​ሪ​ያው ሰፍሮ ነበር።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 26:5
10 交叉引用  

አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቆይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፥ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ሆዱን መታው፥ ሞተም።


ኔርም ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሜልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስባኣልን ወለደ።


ዳዊትም ማልዶ ተነሣ፥ በጎቹንም ለጠባቂ ተወ፥ እሴይም ያዘዘውን ይዞ ሄደ፥ ጭፍራውም ተሰልፎ ሲወጣ ለሰልፍም ሲጮኽ በሰረገሎች ወደ ተከበበው ሰፈር መጣ።


ሳኦልም ዳዊትን ወደ ፍልስጥኤማዊው ሲወጣ ባየው ጊዜ ለሠራዊቱ አለቃ ለአበኔር፦ አበኔር ሆይ፥ ይህ ብላቴና የማን ልጅ ነው? አለው። አበኔርም፦ ንጉሥ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፥ አላውቅም አለ።


ዳዊትም ሰላዮች ሰደደ፥ ሳኦልም ወደዚህ እንደ መጣ በእርግጥ አወቀ።


ስሙ ቂስ የተባለ አንድ ብንያማዊ ሰው ነበረ፥ እርሱም የአቢኤል ልጅ፥ የጽሮር ልጅ፥ የብኮራት ልጅ፥ የብንያማዊው የአፌቅ ልጅ፥ ጽኑዕ ኃያል ሰው ነበረ።


跟着我们:

广告


广告