Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 26:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ሳኦል ዳዊትን፦ ልጄ ዳዊት ሆይ፥ ቡሩክ ሁን፥ ማድረግን ታደርጋለህ፥ መቻልንም ትችላለህ አለው። ዳዊትም መንገዱን ሄደ፥ ሳኦልም ወደ ሰፍራው ተመለሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፣ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ የተባረክህ ሁን፤ ታላቅ ነገር ታደርጋለህ፤ በርግጥም ይከናወንልሃል” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደሚሄድበት ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ቤቱ ተመለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ የተባረክህ ሁን፤ ብዙ ነገር ታደርጋለህ፤ በእርግጥም ይከናወንልሃል” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደሚሄድበት ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ሳኦልም ዳዊትን “ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ! ብዙ ነገርን ታደርጋለህ፤ ይሳካልሃልም” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደ ፈለገበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ቤቱ ተመለሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ቡሩክ ሁን፤ ማድ​ረ​ግን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ መቻ​ል​ንም ትች​ላ​ለህ” አለው። ዳዊ​ትም መን​ገ​ዱን ሄደ፤ ሳኦ​ልም ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 26:25
10 交叉引用  

አለውም፦ ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና።


በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፥ በፍርድም የሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር።


በማኅፀን ውስጥ ወንድሙን በተረከዙ ያዘው፥ በጕልማስነቱም ጊዜ ከአምላክ ጋር ታገለ፥


ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?


በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።


ጠላቱን አግኝቶ በመልካም መንገድ ሸኝቶ የሚሰድድ ማን ነው? ስለዚህ ለእኔ ስላደረግኸው ቸርነት እግዚአብሔር ይመልስልህ።


አሁንም፥ እነሆ፥ አንተ በእርግጥ ንጉሥ እንድትሆን የእስራኤልም መንግሥት በእጅህ እንድትጸና እኔ አውቃለሁ።


ዳዊትም ለሳኦል ማለለት፥ ሳኦልም ወደ ቤቱ ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹም ወደ አምባው ወጡ።


跟着我们:

广告


广告