Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 25:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የሰውዮውም ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢግያ ነበረ፥ የሴቲቱም አእምሮ ታላቅ፥ መልክዋም የተዋበ ነበረ፥ ሰውዮው ግን ባለጌ ነበረ፥ ግብሩም ክፉ ነበረ፥ ከካሌብም ወገን ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የሰውየው ስም ናባል፣ የሚስቱም ስም አቢግያ ነበረ። እርሷም አስተዋይና ውብ ነበረች፤ ባሏ ግን ባለጌና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበረ፤ እርሱም ከካሌብ ወገን ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የሰውየው ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢጌል ነበረ። እርሷም አስተዋይና ውብ ነበረች፤ ባሏ ግን ባለጌና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበረ፤ እርሱም ከካሌብ ወገን ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የሰ​ው​ዬ​ውም ስም ናባል፥ የሚ​ስ​ቱም ስም አቤ​ግያ ነበረ፤ ሴቲ​ቱም ደግና ብልህ፥ መል​ክ​ዋም እጅግ የተ​ዋበ ነበረ፤ ሰው​ዬው ግን ጨካ​ኝና ንፉግ ነበረ፤ ግብ​ሩም ክፉ ነበረ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 25:3
15 交叉引用  

ወደ ግብፅም ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፤ አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ፤


እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዳዘዘው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ቂርያትአርባቅ የምትባለውን ከተማ ድርሻ አድርጎ ሰጠው፥ እርስዋም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።


ስለዚህም በጌታችንና በቤቱ ሁሉ ላይ ክፉ ነገር እንዲመጣ ተቆርጦአልና፥ እርሱ ምናምንቴ ሰው ስለ ሆነ ማንም ሊናገረው አይችልምና የምታደርጊውን ተመልከቺና እወቂ።


በዚህ ምናምንቴ ሰው በናባል ላይ ጌታዬ ልቡን እንዳይጣል እለምናለሁ፥ እንደ ስሙ እንዲሁ እርሱ ነው፥ ስሙ ናባል ነው፥ ስንፍናም አድሮበታል፥ እኔ ባሪያህ ግን ከአንተ የተላኩትን የጌታዬን ጕልማሶች አላየሁም።


ዳዊትም በምድረ በዳ ሳለ፦ ናባል በጎቹን ይሸልታል የሚል ወሬ ሰማ።


እኛም በከሊታውያን ደቡብ፥ በይሁዳም ምድር፥ በካሌብም ደቡብ ላይ ዘመትን፥ ጺቅላግንም በእሳት አቃጠልናት አለ።


跟着我们:

广告


广告