Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 24:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከእርሱም በኋላ ዳዊት ደግሞ ተነሣ፥ ከዋሻውም ወጣ፥ ከሳኦልም በኋላ፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ብሎ ጮኸ፥ ሳኦልም ወደ ኋላው ተመለከተ፥ ዳዊትም ወደ ምድር ተጎንብሶ እጅ ነሣ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚያም ዳዊት ከዋሻው ወጥቶ ሳኦልን፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” ብሎ ጠራው። ሳኦልም ወደ ኋላው ዞር ባለ ጊዜ፣ ዳዊት ወደ መሬት ጐንበስ ብሎ እጅ ሲነሣው ተመለከተ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ዳዊት ሰዎቹን በዚህ ቃል ከለከላቸው፤ በሳኦል ላይ አደጋ እንዲያደርሱበትም አልፈቀደላቸውም። ሳኦልም ከዋሻው ወጥቶ ሄደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ዳዊትም ከዚያ ወጥቶ ሳኦልን በመከተል “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” አለው፤ ሳኦልም መለስ ብሎ ዙሪያውን ሲመለከት ዳዊት በመሬት ላይ ለጥ ብሎ እጅ ነሣውና እንዲህ አለው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዳዊ​ትም በዚህ ቃል ሰዎ​ቹን ከለ​ከ​ላ​ቸው። በሳ​ኦ​ልም ላይ ተነ​ሥ​ተው ይገድ​ሉት ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ቸ​ውም፤ ሳኦ​ልም ከዋ​ሻው ተነ​ሥቶ መን​ገ​ዱን ሄደ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 24:8
11 交叉引用  

አብራምም በግምባሩ ወደቀ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረው፥


ቤርሳቤህም በግምባርዋ በምድር ላይ ተደፍታ ለንጉሡ እጅ ነሣችና “ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘላለም በሕይወት ይኑር!” አለች።


አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።


ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።


ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ፥ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ንጉሥን አክብሩ።


ብላቴናውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከስፍራው በደቡብ አጠገብ ተነሣ፥ በምድርም ላይ በግምባሩ ተደፋ፥ ሦስት ጊዜም ለሰላምታ ሰገደ፥ እየተላቀሱም እርስ በእርሳቸው ተሳሳሙ፥ ይልቁንም ዳዊት እጅግ አለቀስ።


ዳዊትም በዚህ ቃል ሰዎቹን ከለከላቸው፥ በሳኦልም ላይ ይነሡ ዘንድ አልተዋቸውም፥ ሳኦልም ከዋሻው ተነሥቶ መንገዱን ሄደ።


ዳዊትም ሳኦልን አለው፦ እነሆ፥ ዳዊት ክፉ ነገር ይሻብሃል የሚሉህን ሰዎች ቃል ለምን ትሰማለህ?


ሳኦልም የዳዊት ድምፅ እንደ ሆነ አውቆ፦ ልጄ ዳዊት ሆይ፥ ይህ ድምፅህ ነውን? አለው። ዳዊትም፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ድምፄ ነው አለው።


እርሱም፦ መልኩ ምን ዓይነት ነው? አላት። እርስዋም፦ ሽማግሌ ሰው ወጣ፥ መጎናጸፊያም ተጎናጽፎአል አለች። ሳኦልም ሳሙኤል እንደ ሆነ አወቀ፥ በፊቱም ተጎነበሰ፥ በምድርም ላይ እጅ ነሣ።


跟着我们:

广告


广告