Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 24:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የዳዊትም ሰዎች፦ እነሆ፥ ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ በዓይንህም ደስ የሚያሰኝህን ታደርግበታለህ ብሎ እግዚአብሔር የነገርህ ቀን፥ እነሆ፥ ዛሬ ነው አሉት። ዳዊትም ተነሥቶ የሳኦልን መጎናጸፊያ ዘርፍ በቀስታ ቆረጠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የዳዊት ሰዎችም ዳዊትን፣ “እግዚአብሔር፣ ‘የወደድኸውን ታደርግበት ዘንድ ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ’ ብሎ ለአንተ የተናገረው ቀን ዛሬ ነው” አሉት። ዳዊትም በልቡ እየተሳበ ሄዶ የሳኦልን ልብስ ጫፍ ማንም ሳያውቅ ቈርጦ ወሰደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ሳኦልም በመንገድ ዳር ወዳለው ወደ አንድ የበጎች ማደሪያ በደረሰ ጊዜ፥ ዋሻ አግኝቶ ወገቡን ሊሞክር ወደዚያ ገባ። ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ተከታዮቹም ዳዊትን “እነሆ፥ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖልሃል! እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ እንደሚጥልልህ ነግሮሃል፤ እነሆ፥ አሁን በጠላትህ ላይ የፈለግኸውን ማድረግ ትችላለህ!” አሉት፤ ዳዊትም በልቡ እየተሳበ በመቅረብ ሳኦል ሳያውቅ ከልብሱ ጫፍ ላይ ቈርጦ ወሰደ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በመ​ን​ገ​ድም አጠ​ገብ ወዳ​ሉት የበ​ጎች ማደ​ሪ​ያ​ዎች ወጣ፤ በዚ​ያም ዋሻ ነበረ፤ ሳኦ​ልም ወገ​ቡን ይሞ​ክር ዘንድ ወደ​ዚያ ዋሻ ገባ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ከዋ​ሻው በው​ስ​ጠ​ኛው ቦታ ተቀ​ም​ጠው ነበር።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 24:4
13 交叉引用  

የኢያቡስቴንም ራስ ይዘው ወደ ዳዊት ወደ ኬብሮን መጡ፥ ንጉሡንም፦ ነፍስህን ይሻ የነበረው የጠላትህ የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ እነሆ፥ እግዚአብሔርም ዛሬ ከሳኦልና ከዘሩ ለጌታችን ለንጉሥ ተበቀለለት አሉት።


በድንኳኔ የሚኖሩ ሰዎች፦ በከብቱ ሥጋ ያልጠገበ ማን ይገኛል? ብለው እንደ ሆነ፥


ባይሸምቅበትም፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ድንገት በእጁ ቢጥለው፥ የሚሸሽበት ስፍራ እኔ አደርግልሃለሁ።


ዳዊትም ከዚያ ተነሣ ወደ ዓዶላም ዋሻ ኮበለለ፥ ወንድሞቹና የአባቱም ቤት ሰው ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ ወደዚያ ወረዱ።


የአባቴ የሳኦል እጅ አታገኝህምና አትፍራ፥ አንተም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆናለህ፥ እኔም ከአንተ በታች ሁለተኛ እሆናለሁ፥ ይህን ደግሞ አባቴ ሳኦል ያውቃል አለው።


ሳኦልም ዳዊት ወደ ቅዒላ እንደ መጣ ሰማ፥ ሳኦልም፦ መዝጊያና መወርወሪያ ወዳለባት ከተማ ገብቶ ተገኝቶአልና እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶታል አለ።


እነሆ፥ ዛሬ በዋሻው ውስጥ እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ እንደ ሰጠህ ዓይንህ አይታለች፥ አንተንም እንድገድልህ ሰዎች ተንገሩኝ፥ እኔ ግን፦ በእግዚአብሔር የተቀባ ነውና እጄን በጌታዬ ላይ አልዘረጋም ብዬ ራራሁልህ።


እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ አልገደልኸኝምና ለእኔ መልካም እንዳደረግህልኝ አንተ ዛሬ አሳየኸኝ።


ዛሬም እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶህ ሳለ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ አልወደድሁምና ለሁሉ እያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ ጽድቁና እንደ እምነቱ ፍዳውን ይክፈለው።


跟着我们:

广告


广告